YouVersion Logo
Search Icon

ኢያሱ 12

12
የተሸነፉ ነገሥታት ስም ዝርዝር
1እንግዲህ እስራኤላውያን ድል ያደረጓቸውና ከዮርዳኖስ ማዶ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የዓረባን ክፍል በሙሉ ይዞ፣ ከአርኖን ሸለቆ እስከ አርሞንዔም ተራራ የሚዘልቀውን ግዛታቸውን የወሰዱባቸው ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤
2መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣
ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።
3እንዲሁም ከኪኔሬት ባሕር#12፥3 “ገሊላ” ናት። እስከ ሙት#12፥3 የሙት ባሕር፣ የጨው ባሕርም ይባላል። ባሕር ያለውን ምሥራቃዊውን ዓረባ፣ እስከ ቤት የሺሞትና ከዚያም በስተ ደቡብ እስከ ፈስጋ ተራራ ግርጌ ድረስ ገዝቷል።
4መቀመጫውን በአስታሮትና በኤድራይ አድርጎ የገዛውና ከመጨረሻዎቹ ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነው የባሳን ንጉሥ ዐግ፣
5የአርሞንዔምን ተራራ፣ ሰልካንን፣ ባሳንን ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ድንበሮች እንዲሁም ከገለዓድ እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ወሰን ድረስ ገዝቷል።
6 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴና እስራኤላውያን እነዚህን ድል አደረጉ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴም ምድራቸውን ለሮቤል፣ ለጋድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርጎ ሰጣቸው።
7እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው። 8ይህም ተራራማው አገር፤ በስተ ምዕራብ ያለው የኰረብታ ግርጌ፣ ዓረባ፣ የተራራው ሸንተረሮች፣ ምድረ በዳውና ነጌብ ማለት የኬጢያውያን፣ የአሞራውያን፣ የከነዓናውያን፣ የፌርዛውያን፣ የኤዊያውያንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው፤ ነገሥታቱም እነዚህ ናቸው፤
9የኢያሪኮ ንጉሥ፣ አንድ፤
ቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፣ አንድ፤
10የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ አንድ፤
የኬብሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
11የየርሙት ንጉሥ፣ አንድ፤
የለኪሶ ንጉሥ፣ አንድ፤
12የዔግሎን ንጉሥ፣ አንድ፤
የጌዝር ንጉሥ፣ አንድ፤
13የዳቤር ንጉሥ፣ አንድ፤
የጌድር ንጉሥ፣ አንድ፤
14የሔርማ ንጉሥ፣ አንድ፤
የዓራድ ንጉሥ፣ አንድ፤
15የልብና ንጉሥ፣ አንድ፤
የዓዶላም ንጉሥ፣ አንድ፤
16የመቄዳ ንጉሥ፤ አንድ፤
የቤቴል ንጉሥ፣ አንድ፤
17የታጱዋ ንጉሥ፣ አንድ፤
የኦፌር ንጉሥ፣ አንድ፤
18የአፌቅ ንጉሥ፣ አንድ፤
የለሸሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
19የማዶን ንጉሥ፣ አንድ፤
የሐጾር ንጉሥ፣ አንድ፤
20የሺምሮን ሚሮን ንጉሥ፣ አንድ፤
የአዚፍ ንጉሥ፣ አንድ፤
21የታዕናክ ንጉሥ፣ አንድ፤
የመጊዶ ንጉሥ፣ አንድ፤
22የቃዴስ ንጉሥ፣ አንድ፤
በቀርሜሎስ የሚገኘው የዮቅንዓም ንጉሥ፣ አንድ፤
23በዶር ኰረብታ#12፥23 ወይም፣ “ናፎት ዳር” ማለት ነው። የሚገኘው የዶር ንጉሥ፣ አንድ፤
በጌልገላ የሚገኘው የጎይም ንጉሥ፣ አንድ፤
24የቲርሳ ንጉሥ፣ አንድ።
እነዚህ በድምሩ ሠላሳ አንድ ነገሥታት ናቸው።

Currently Selected:

ኢያሱ 12: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in