YouVersion Logo
Search Icon

ኢዮብ 6

6
ኢዮብ
1ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2“ምነው ሐዘኔ በተመዘነ!
መከራዬም ሚዛን ላይ በተቀመጠ!
3ከባሕር አሸዋ ይልቅ በከበደ፣
ኀይለ ቃሌም ባላስገረመ ነበር!
4ሁሉን የሚችል አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤
መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤
የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል።
5የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣
በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?
6የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን?
ወይስ የዕንቍላል#6፥6 በዕብራይስጥ የዚህ ሐረግ ትርጕም አይታወቅም። ውሃ ጣዕም አለውን?
7እንዲህ ዐይነቱን ምግብ እጸየፋለሁ፤
ለመንካትም አልፈልግም።
8“ምነው ልመናዬ በተመለሰልኝ፤
እግዚአብሔር የምመኘውን በሰጠኝ፤
9እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣
ምነው እጁ በተፈታ!
10ፋታ በማይሰጥ ሕመም ውስጥ እየተደሰትሁ፣
ይህ መጽናኛ በሆነልኝ ነበር፤
የቅዱሱን ትእዛዝ አልጣስሁምና።
11“አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣
እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?
12የድንጋይ ጕልበት አለኝን?
ሥጋዬስ ናስ ነውን?
13ያልተሳካልኝ ሰው ነኝና፣
ራሴን ለመርዳት ምን ጕልበት አለኝ?
14“ለወዳጁ በጎነት የማያሳይ ሰው፣
ሁሉን የሚችለውን አምላክ መፍራት ትቷል።
15ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣
ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤
16በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤
ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤
17በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤
በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።
18ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤
ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ።
19የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉ፤
የሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ።
20ርግጠኞች ሆነው ስለ ነበር ተሰቀቁ፤
እዚያ ደረሱ፣ ግን ዐፈሩ።
21አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፤
መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ።
22ለመሆኑ፣ ‘ስለ እኔ ሆናችሁ አንድ ነገር ስጡልኝ፣
በዕዳ የተያዘብኝንም በሀብታችሁ አስለቅቁልኝ!’ ብያለሁን?
23ወይስ፣ ‘ከጠላት አስጥሉኝ፣
ከጨካኝም እጅ ተቤዡኝ’ አልኋችሁን?
24“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤
ምኑ ላይ እንደ ተሳሳትሁ ጠቍሙኝ።
25የቅንነት ቃል ምንኛ ኀያል ነው!
የእናንተ ክርክር ግን ምን ፋይዳ አለው?
26የተናገርሁትን ለማረም፣
ተስፋ የቈረጠውንም ሰው ቃል እንደ ነፋስ ለመቍጠር ታስባላችሁን?
27በድኻ ዐደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁን?
ወይስ ወዳጃችሁን ትሸጣላችሁን?
28“አሁን ግን ፈቃዳችሁ ቢሆን ወደ እኔ ተመልከቱ፤
ፊት ለፊት እዋሻችኋለሁን?
29መለስ በሉ፤ ፍርደ ገምድል አትሁኑ፤
ጽድቄ ጸንታ ቆማለችና መለስ ብላችሁ አስተውሉ።
30ክፋት በአንደበቴ አለን?
አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?

Currently Selected:

ኢዮብ 6: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in