YouVersion Logo
Search Icon

ኢዮብ 36

36
1ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤
2“በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤
ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ።
3ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤
ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደ ሆነ እገልጻለሁ።
4ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤
በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋር ነው።
5“እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤
ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።
6ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤
ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።
7ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤
ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤
ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።
8ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣
በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣
9በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣
ተግባራቸውን ይነግራቸዋል።
10ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤
ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዝዛቸዋል።
11ታዝዘው ቢያገለግሉት፣
ቀሪ ዘመናቸውን በተድላ፣
ዕድሜያቸውንም በርካታ ይፈጽማሉ።
12ባይሰሙ ግን፣
በሰይፍ#36፥12 ወይም፣ ወንዙን ያቋርጣሉ ይጠፋሉ፤
ያለ ዕውቀትም ይሞታሉ።
13“ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ፣ ቍጣን ያስተናግዳሉ፤
በሰንሰለት ባሰራቸውም ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ አይጮኹም።
14በቤተ ጣዖት ውስጥ ዝሙት በሚፈጽሙት መካከል፣
ገና በወጣትነታቸው ይቀጫሉ።
15ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤
በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።
16“አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣
ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣
ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።
17አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኗል፤
ፍርድና ብይን ይዘውሃል።
18ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣
የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።
19ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣
ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?
20ሰዎች ከቤታቸው#36፥20 በዕብራይስጥ ከ18-20 ያለው ክፍል ትርጕሙ በትክክል አይታወቅም። የሚወሰዱበትን፣
ሌሊት አትመኝ።
21ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣
ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
22“እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሏል፤
እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?
23እርሱን መንገድ የሚመራው፣
ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?
24ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣
የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።
25ሰው ሁሉ አይቶታል፤
ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።
26እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው!
የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።
27“የውሃን ነጠብጣብ ወደ ላይ ያተንናል፤
መልሶም በዝናብ መልክ በጅረቶች ላይ ያወርዳል፤
28ደመናት ጠል ያንጠባጥባሉ፤
ዶፍም በሰው ላይ ይወርዳል።
29ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣
ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጕድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
30መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት፤
የባሕሩንም ወለል ይሸፍናል።
31እርሱ ሕዝብን የሚያስተዳድረው፣#36፥31 ወይም፣ የሚያስተዳድረው ምግብንም አትረፍርፎ የሚሰጣቸው
በዚህ መንገድ ነው።
32እጆቹን በመብረቅ ይሞላቸዋል፤
ዒላማውንም እንዲመታ ያዝዘዋል።
33ነጐድጓዱ ውሽንፍር እንደሚከተለው ያመለክታል፤
ከብቶችም እንኳ መምጣቱን ይጠቍማሉ።

Currently Selected:

ኢዮብ 36: NASV

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in