YouVersion Logo
Search Icon

ዮሐንስ 15:1-4

ዮሐንስ 15:1-4 NASV

“እውነተኛው የወይን ተክል እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው። እርሱም በእኔ ያለውን፣ የማያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ቈርጦ ይጥለዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን የበለጠ እንዲያፈራ ይገርዘዋል። ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ አሁን ንጹሓን ናችሁ። በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ እኖራለሁ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ካልሆነ በቀር ብቻውን ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፤ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ልታፈሩ አትችሉም።

Video for ዮሐንስ 15:1-4

Free Reading Plans and Devotionals related to ዮሐንስ 15:1-4