ሆሴዕ 3
3
የሆሴዕ ከሚስቱ ጋር መታረቅ
1 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “እርሷ በሌላ ሰው የምትወደድ አመንዝራ ብትሆንም፣ አሁንም ሂድና ሚስትህን ውደዳት፤ ወደ ሌሎች አማልክት ዘወር ቢሉና ለእነርሱም የተቀደሰውን የዘቢብ ጥፍጥፍ ቢወድዱም፣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንደ ወደዳቸው አንተም እርሷን ውደዳት።”
2ስለዚህ በዐሥራ አምስት ሰቅል ጥሬ ብርና በአንድ ቆሮስ ተኩል መስፈሪያ ገብስ ገዛኋት። 3እኔም፣ “ከእኔ ጋር ብዙ ቀን ተቀመጪ፤#3፥3 ወይም ቈዪ አታመንዝሪ ወይም ሌላ ሰው አትውደጂ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” ብዬ ነገርኋት።
4እስራኤላውያን ለብዙ ዘመን ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፣ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዐምደ ጣዖት፣ ያለ ኤፉድና ያለ ጣዖት ምስል ይኖራሉና። 5ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ተመልሰው አምላካቸውን እግዚአብሔርንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤ በመጨረሻውም ዘመን በመንቀጥቀጥ ወደ እግዚአብሔርና ወደ በረከቱ ይመጣሉ።
Currently Selected:
ሆሴዕ 3: NASV
Highlight
Share
Copy
Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.