ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ብትቀበል፥
ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት፥
ጆሮህ ጥበብን ትሰማለች፥
ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ።
ልብህንም ልጅህን ለመምከር ታቀርባለህ፥
ጥበብን ብትጠራት፥ ቃልህንም ለማስተዋል ብትሰጥ፥
ዕውቀትንም በታላቅ ቃል ብትፈልጋት፥
እርስዋንም እንደ ብር ብትፈልጋት፥
እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፤
የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥
አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ።