1
ወደ ሮም ሰዎች 14:17-18
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ጽድቅ፥ ሰላምና ደስታ ነው እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም። በዚህ ሁኔታ ክርስቶስን የሚያገለግል ሰው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።
Compare
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:17-18
2
ወደ ሮም ሰዎች 14:8
ብንኖር ለጌታ እንኖራለን፤ ብንሞትም ለጌታ እንሞታለን፤ ስለዚህ ብንኖርም፥ ብንሞትም የጌታ ነን።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:8
3
ወደ ሮም ሰዎች 14:19
ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:19
4
ወደ ሮም ሰዎች 14:13
ስለዚህ አንዳችን በአንዳችን ላይ አንፍረድ፤ ነገር ግን ማንም ሰው በወንድሙ መንገድ መሰናክል ወይም እንቅፋት ላለማኖር ይጠንቀቅ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:13
5
ወደ ሮም ሰዎች 14:11-12
ምክንያቱም፦ “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤ ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል። ስለዚህ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ሥራ በእግዚአብሔር ፊት ቀርበን መልስ እንሰጣለን።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:11-12
6
ወደ ሮም ሰዎች 14:1
በእናንተ መካከል በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በግል ሐሳቡ ላይ ክርክር አታንሡ።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:1
7
ወደ ሮም ሰዎች 14:4
ታዲያ፥ በሌላ ሰው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ የጌታው ጉዳይ ነው። እንዲያውም እግዚአብሔር ሊያቆመው ስለሚችል ጸንቶ ይቆማል።
Explore ወደ ሮም ሰዎች 14:4
Home
Bible
Plans
Videos