1
ትንቢተ ኤርምያስ 18:6
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ሸክላ ሠሪው ሸክላውን በፈለገው ዐይነት እንደሚሠራው፥ እኔስ በእናንተ ላይ የፈለግኹትን ማድረግ አልችልምን? የሸክላው ጭቃ በሸክላ ሠሪው እጅ እንደሚገኝ እናንተም፥ በእኔ እጅ ናችሁ።
Compare
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 18:6
2
ትንቢተ ኤርምያስ 18:7-8
እኔ አንድን ሕዝብ ወይም መንግሥት፥ ‘እነቅላለሁ ወይም ሰባብሬ አጠፋለሁ’ ብዬ በተናገርኩ ጊዜ፥ ያ ሕዝብ ተጸጽቶ ከክፋቱ የሚመለስ ከሆነ፥ አመጣበታለሁ ብዬ ያቀድኩትን ክፉ ነገር አላደርግበትም።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 18:7-8
3
ትንቢተ ኤርምያስ 18:9-10
በሌላ በኩል ደግሞ እኔ አንድን ሕዝብ ወይም መንግሥት ‘እተክላለሁ ወይም እገነባለሁ’ በምልበት ጊዜ፥ ያ ሕዝብ ለእኔ የማይታዘዝና ክፋትንም የሚያደርግ ሆኖ ከተገኘ ላደርግለት ያቀድኩትን መልካም ነገር አላደርግለትም።
Explore ትንቢተ ኤርምያስ 18:9-10
Home
Bible
Plans
Videos