1
ኢሳይያስ 9:6
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
Compare
Explore ኢሳይያስ 9:6
2
ኢሳይያስ 9:2
በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትም ብርሃን ወጣላቸው።
Explore ኢሳይያስ 9:2
3
ኢሳይያስ 9:7
ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።
Explore ኢሳይያስ 9:7
4
ኢሳይያስ 9:5
የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።
Explore ኢሳይያስ 9:5
5
ኢሳይያስ 9:1
ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤
Explore ኢሳይያስ 9:1
6
ኢሳይያስ 9:3
ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
Explore ኢሳይያስ 9:3
7
ኢሳይያስ 9:4
ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
Explore ኢሳይያስ 9:4
Home
Bible
Plans
Videos