1
መክብብ 2:26
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
Compare
Explore መክብብ 2:26
2
መክብብ 2:24-25
ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት፣ በሥራውም ከመርካት ሌላ የሚሻለው ነገር የለውም፤ ይህም ደግሞ ከአምላክ እጅ እንደሚሰጥ አየሁ፤ ከርሱ ዘንድ ካልሆነ ማን መብላትና መደሰት ይችላል?
Explore መክብብ 2:24-25
3
መክብብ 2:11
ሆኖም እጆቼ የሠሩትን ሁሉ፣ ለማግኘትም የደከምሁትን ድካም ሁሉ ሳስብ፣ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነበር፤ ከፀሓይ በታች ምንም ትርፍ አልነበረም።
Explore መክብብ 2:11
4
መክብብ 2:10
ዐይኔ የፈለገውን ሁሉ አልከለከልሁትም፤ ለልቤም ምድራዊ ደስታን አልነፈግሁትም፤ ልቤ በሠራሁት ሁሉ ደስ አለው፤ ይህም የድካሜ ሁሉ ዋጋ ነበረ።
Explore መክብብ 2:10
5
መክብብ 2:13
ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ ሁሉ፣ ጥበብም ከሞኝነት እንደሚበልጥ ተመለከትሁ።
Explore መክብብ 2:13
6
መክብብ 2:14
የጠቢብ ሰው ዐይኖች ያሉት በራሱ ውስጥ ነው፤ ሞኝ ግን በጨለማ ውስጥ ይራመዳል፤ ሆኖም የሁለቱም ዕድል ፈንታ፣ አንድ መሆኑን ተገነዘብሁ።
Explore መክብብ 2:14
7
መክብብ 2:21
ምክንያቱም ሰው ሥራውን በጥበብ፣ በዕውቀትና በብልኀት ሠርቶ፣ ከዚያ ያለውን ሁሉ ለሌላ ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። ይህም ደግሞ ከንቱና ትልቅ ጕዳት ነው።
Explore መክብብ 2:21
Home
Bible
Plans
Videos