1
መክብብ 1:18
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ጥበብ ሲበዛ፣ ትካዜ ይበዛልና፤ ዕውቀት ሲጨምርም ሐዘን ይበዛል።
Compare
Explore መክብብ 1:18
2
መክብብ 1:9
የነበረው ነገር እንደ ገና ይሆናል፤ የተደረገውም ተመልሶ ይደረጋል፤ ከፀሓይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም።
Explore መክብብ 1:9
3
መክብብ 1:8
ሰው መናገር ከሚችለው በላይ፣ ነገሮች ሁሉ አድካሚ ናቸው፤ ዐይን ከማየት አይጠግብም፤ ጆሮም በመስማት አይሞላም።
Explore መክብብ 1:8
4
መክብብ 1:2-3
“የከንቱ ከንቱ፤” ይላል ሰባኪው፤ “ሁሉም ነገር ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ ነው።” ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?
Explore መክብብ 1:2-3
5
መክብብ 1:14
ከፀሓይ በታች የተደረገውን ነገር ሁሉ አየሁ፤ ሁሉም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
Explore መክብብ 1:14
6
መክብብ 1:4
ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
Explore መክብብ 1:4
7
መክብብ 1:11
የቀድሞ ነገሮች መታሰቢያ የላቸውም፤ ወደ ፊት የሚመጡትም ቢሆኑ፣ ከእነርሱ በኋላ በሚተኩት አይታወሱም።
Explore መክብብ 1:11
8
መክብብ 1:17
ከዚያም የጥበብንና የእብደትን፣ የሞኝነትንም ነገር ለመገንዘብ ራሴን አተጋሁ፤ ይህም ነፋስን እንደ መከተል መሆኑን ተረዳሁ።
Explore መክብብ 1:17
Home
Bible
Plans
Videos