ታሪካዊ

ታሪካዊ

365 ቀናት

የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን በጥንት እስራኤል ግዜ ሆነው ቢያነቡት ምን ይመስል እንደነበር አስበውት ያውቃሉ? የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትንስ ወዲያው እንደተፃፉ አንብበውት ቢሆን? በዚህ እቅድ ውስጥ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በጥንት እስራኤል የእብራይስጥ መጻሕፍት ቅደም ተከተል መሰረት የተዘጋጁ ናቸው። በሕግ መጻሕፍት በመጀመር የትንቢት መጻሕፍትን ፣ የታሪክ መጻሕፍትን እንዲሁም የጥበብ መጻሕፍትን በማስከተል ይጨርሳል። የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ቅደም ተከተል ደግሞ መጻሕፍቶቹ የተፃፉባቸውን ግዜያት በማጥናት የተመሰረተ ነው። እነዚህ ጥናቶች የመጻሕፍቶቹን ቅደም ተከተል በማያዳግም ሁኔታ ለመወሰን የሚያበቁ ባይሆንም ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትዎት ግን እንደ መነሻ በመሆን ያገለግላል።.

ይህ የንባብ እቅድ የቀረበው በ"ብሉ ሌተር መጽሐፍ ቅዱስ" ነው።.
More from Blue Letter Bible