ወደ ቆላስይስ ሰዎችናሙና
የመሪዎች ስብስቦች የሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌል በጣም ቀላል ነው በማለት የቆላስይስን ቤተ ክርስቲያን እየከፋፈሉ ናቸው፡፡ የቆላስይስ ሰዎች በእርግጥ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ሙላትና ካልተገቡ የትናንት ማንነታቸው ነፃ ለመውጣት መለማመድ ከፈለጉ በዙሪያቸው ካሉ የሀይማኖት ልምዶችም መዋስም ያስፈልጋቸዋል፡፡ ጳውሎስ ግን ቁርጥ ባለ መልኩ በምንም ዓይነት ሁኔታ ኢየሱስን መከተል ፣ እግዚአብሔርን መለማመድና ካልተገቡ ልምምዶች ነፃ መውጣት ከፈለጉ ሁሉም በኢየሱስ በኩል ሆኗል ብሎ ይደመድማል፡፡
አንዱ ቡድን ከኢየሱስ በተጨማሪ በሌሎች መንፈሳዊ ሀይላት መማረክ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅና ለመንፈሳዊ ሙላት ዋስትናን ይሰጣል ብለው ይላሉ፡፡ ጳውሎስእነዚህአደጋዎችጠያቂዎችንወደኃጢአተኛወይምተራበሆኑመንፈሳዊኃይሎችመጠመድ አለባቸውብሏል፡፡ ከዚህም በላይ የእግዚአብሔር ሀይል ሙላት ለቆላሲይስ ሰዎች አንዴ ተሰጥቷቸዋል ይላል፡፡ ኢየሱስ በመካከላቸው ይኖራል፡፡ እግዚአብሔርን በሙላት ለመለማመድ ምንም ዓይነት የሌሎች መንፈሳዊ ባህሎች መሻት አያስፈልግም፡፡
አይሁድ የሆኑ ቡድኖች ደግሞ ክፉ ነገሮቻችሁን በመገረዝ ቆርጣችሁ በማስወገድ ለእግዚአብሔር መሆናችሁን ማረጋገጥ ትችላላችሁ ብለው ይላሉ፡፡ ጳውሎስ ግን ኢየሱስ ታላቁን ግርዛት አንዴ ፈፅሞታል ይለናል፡፡ በጥምቀት መላ አካላቸው ከኢየሱስ ጋር ይቀበራል፤ በዚህም ምክንያት መላ እኛነታችን እግዚአብሔር ከሞት ሲያስነሳን በመቃብሩ ቀርቷል፡፡ ክፉው ማንነታችን ከእኛ ላይ የተወገደው በቢላ ሳይሆን በኢየሱስ መስቀል ነው፡፡ አንዴ ይቅር ተብለናልና ለእግዚአብሔር ሌላ ማስረጃ ለማቅረብ አትሞክሩ፡፡
ግን አሁንም ሌሎች የሚሉት “ጥሩ” የሚባሉት ክርስቲያኖች የተፈቀደውን በልተው በሰንበት ያርፉ ነበር፡፡ የተመረጡ ክርስቲያኖች ደግሞ ስለ ፖለቲካ የሆነ አመለካከት ነበራቸው፡፡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ደግሞ በመፆም ራዕይ ነበራቸው፡፡ ጳውሎስ ግን ምንም እንኳን እኚህ ሁሉ መልካም የሚመስሉ ቢመስልም ውጤታቸው እኛን መከፋፈል ሲሆን በምንም መልኩ እኛን ከትናንት ብለሹ ተግባራችን ነፃ ሊያወጡን ወይም የእግዚአብሔርን ሙላት በፍፁም ሊሰጡን አይችሉም ይለናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፖለቲካው እየፈለጉት ያለው፣ የሰንበት ህግጋት እንዲሁም ራዕይ አንድ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የኢየሱስ ከሞት መነሳት ወይም ትንሳኤ የፖለቲካ ሀይልን ትጥቅ አስፈትቷል፡፡ ሰንበት ስለ ኢየሱስ ነው፡፡ በአእምሮአችን የሚመላለሱት ራዕይዎች እኛን አይለውጡንም፤ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን ራስ የሆነው እንደገና በመልኩ ትንሳኤ ሊሰጠን ይችላል፡፡
የእግዚአብሔር ሰዎች የወረደውን የሰውን ፍልስፍና፣ ሀይላትና ልማድን ከመመልከት ይልቅ ቀና ብለው ከሞት የተነሳውንና በሰማያት በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን ኢየሱስን መመልከት እንዲሁም በእርሱ ያላቸውን አዲስ ህይወት ማየት አለባቸው፡፡ ኢየሱስ ብቻውን ህዝቡን ሙሉና ነፃ ያደርጋቸዋል፡፡ የቆላስይስ ሰዎች ሕይወት ከኢየሱስ ጋር በሰማይ ነው፣ ይህ ማለት ምድራዊ የሆኑትን ነገሮች ለመግደልና እንደ አዲስ ፍጥረትም አዲስ ማንነታቸውን ለመልበስ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ተቀብለዋል ማለት ነው፡፡ ቅናትናመከፋፈልከተሞሉ ልቦች ይልቅደግነትንናይቅርታንመልበስይችላሉ፡፡ እነርሱ ኢየሱስን የሚፈልጉት ሙሉ የሆነ መንፈሳዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድና ካልተገቡ ትናንቶቻቸው ነፃ ለመውጣት ብቻ ነው፡፡
ጳውሎስ የዚህን የደብዳቤ ክፍል የሚቋጨው የቆላሲይስ ሰዎች አንድ እንዲሆኑ በማበረታታት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሙላትና ከክፋት ነጻ መውጣት በኢየሱስ ብቻ መሰጠቱ በተለምዶ የማይስማሙ ሰዎችን አንድነት ይፈጥራል፡፡ በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔርን ለማስደሰት አይሁዳዊና አይሁዳዊ ያልሆነ መንገድ የለም፡፡ ጨዋነታችንን የምናረጋግጥበት የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ የሚባል መንገድም የለም፡፡ ኢየሱስ ብቻ አለ፡፡ በእርሱ እንሞታለን ሁላችንም በእርሱ እንነሳለን፡፡
የኢየሱስመስቀልናትንሳኤኢየሱስብቻሙሉናነጻእንደሚያደርጋቸውአንድ በሚያደርግ ተስፋአዲስ ሉል አቀፍና ዓለም ዓቀፋዊ የእግዚአብሔርን ህዝብ ፈጥሯል፡፡ ይህ እውነት በእኛ እንዲኖር በፈቀድን ልክና ይህንኑ እውነት ወደ ሌሎች ባስተጋባን መጠን ሁላችንን ወዳዳነን እግዚአብሔር በምስጋና አንድ መሆን እንችላለን፡፡
ጓደኞችህምበጾምወይምበመንፈሳዊልምምዶችከእግዚአብሔርጋርበሚኖራቸውግንኙነትጥልቅሙላትንእንዲለማመዱመፈለግምምንምዓይነት ስህተትየለውም፡፡ እንዲሁም ራስህን ከአንዳንድ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ጋር ማጣጣምህና አልያም መከላከልህ ምንም ስህተት የለውም፡፡ ስህተት የሚሆነው የአንተ እምነት ከኢየሱስ መስቀል የበለጠ ሙላትና ነፃነትን የሚሰጥ ዓይነት አድርገህ ማስተማር፣ ማመላከትና ማንፀባረቅ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ የበላይነት ስሜት አንድነትን አያመጣም፡፡ ይልቅበኢየሱስበኩል በእግዚአብሔርጸጋየዳኑሰዎችአንድበሚያደርጋቸውበጌታስምሁሉንምነገርማድረግአለባቸው፤ እናምየኢየሱስኃይልእንጂየሚያድነንየእኛእምነትአይደለምና እግዚአብሔርይመስገን፡፡
መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን የሰጠንን እግዚአብሔር ታይ ዘንድ ዓይኖችህን ያበራ ዘንድ እፀልይልሃለሁ፡፡ ለእግዚአብሔር ሙላትና ከክፋት ነፃ ለመውጣት መለማመድ የሚገባን ብቸኛው አካል ኢየሱስ መሆኑን ማየት ይሁንልህ፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ
ይህ የአራት ቀናት ዕቅድ ጳውሎስ ወደ ቆላስይስ ሰዎች የፃፈውን ደብዳቤ ይዳስሳል፤ ይኸውም ዓለማትን የፈጠረውና የሰውን ልጅ የታደገው ከሁሉ በላይና ለሁሉ የሚበቃው ኢየሱስ መሆኑን በማስታወስ የሀሰት ትምህርቶችን በመሞገት ነው፡፡ ጳወሎስ ጨምሮም ስለ ቤተሰብ ግንኙነት፣ ፀሎት፣ ቅዱስ አኗኗር እና በፍቅር መታሰር ምን እንደሆነ ተግባራዊ ጥበብን ይሰጣል፡፡
More
ይህንን እቅድ ስላቀረበልን Spoken Gospel ን ልናመሰግን እንወዳለን። ለበለጠ መረጃ፣እባክዎ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ http://www.spokengospel.com/