BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎችናሙና

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ቀን {{ቀን}} ከ28

ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን ህጎች መካከል ከሁሉ የሚበልጠው ህግ የቱ እንደሆነ በተጠየቀ ጊዜ መልስ የሰጠው ሼማ በመባል ከሚታወቀው ጥንታዊ ጸሎት በመጥቀስ ነው፦ "እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ ውደድ።" ይህ ብቻ ግን አይደለም። ኢየሱስ በፍጥነት ሌላ የብሉይ ኪዳን ትዕዛዝ ከሁሉ እንደሚበልጥ ጨምሮ ተናግሯል፦ "ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ።" ስለዚህ ከሁሉ የሚበልጠው ህግ የቱ ነው? ለኢየሱስ ሁለቱም ወሳኝ ትዕዛዛት ናቸው፤ ምክንያቱም ያለሁለተኛው ትዕዛዝ የመጀመሪያውን ትዕዛዝ ማክበር አይችልም። አይለያዩም። አንድ ሰው ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር የሚገለጠው ለሌሎች ባለው ፍቅር ነው።

ያንብቡ፦

ማርቆስ 12÷29-31፣ ዘዳግም 6÷5፣ ዘሌዋውያን 19÷18

ምልከታዎን ያስፍሩ፡

ኢየሱስ ከብሉይ ኪዳን ከጠቀሰ በኋላ ለሚናገረው ነገር ትኩረት ይስጡ። ንግግሩን ሲያስተውሉ የተፈጠረብዎት ጥያቄዎች፣ ሀሳቦች ወይም ስሜቶች ምንድን ናቸው?

ከዘዳግምና ዘሌዋውያን የተወሰዱትን ምንባቦች ይከልሱ። ምን ያስተውላሉ? ዛሬ ይህ በእርስዎ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?

ምልከታዎን ከልብ ወደመነጨ ጸሎት ይቀይሩት።

ቀን 22ቀን 24

ስለዚህ እቅድ

BibleProject | የዘወረደ ምልከታዎች

ባይብል ፕሮጀክት የዘወረደ ተከታታይ ትምህርቶችን ያዘጋጀው ግለሰቦች፣ ቡድኖች እንዲሁም ቤተሰቦች ዘወረደን፣ ማለትም የኢየሱስን ወደ ምድር መምጣት እንዲያከብሩ ለማነሳሳት ነው። ተስፋ፣ ሰላም፣ ሀሴት እና ፍቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጉማቸው ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች እንዲያጤኑ ለማገዝ እንዲጠቅም፣ ይህ የአራት ሳምንት የጥናት እቅድ የአኒሜሽን ቪዲዮዎችን፣ አጫጭር ማጠቃለያዎችን እና ሃሳብ ጫሪ ጥያቄዎችን አካቷል። እነዚህ አራት መንፈሳዊ እሴቶች እንዴት በኢየሱስ በኩል ወደ አለም እንደመጡ ለመረዳት፣ ይህን የጥናት እቅድ ይምረጡ።

More

BibleProject መጽሐፍ ቅዱስን የበለጠ እንዲያውቁት የሚያግዝዎ ነጻ አገልግሎት ነው። አገልግሎታችንን የምናከናውነው፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወገኖች በሚያደርጉልን ቸርነት የሞላበት ስጦታ ነው። ስለ ባይብል ፕሮጀክት የበለጠ ለማወቅ ድረ ገጻችንን የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይጎብኙ፦ bibleproject.com/Amharic