ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና
የዮሐንስ ወንጌል መግቢያ
ይህ መጽሐፍ የተጻፈው ከኢየሱስ 12 ቱ ሐዋርያት መካከል በነበረው ዮሐንስ ነው። ጴጥሮስና ያዕቆብን ጨምሮ ዮሐንስ የኢየሱስ “ቅርብ ሰዎች” ውስጥ ከሚባሉት ናቸው። እነዚህ ሶስት ሰዎች ለኢየሱስ ቅርብ ነበሩ። የሐንስና ወንድሙ ያዕቆብ “የነጎድጓድ ልጆች" ተብለውም ይጠራሉ።
በርካታ ምሁራን ዮሐንስ መጽሐፉን ከ 85-90 ዓም ባለው ግዜ ውስጥ እንደጻፈው ይናገራሉ ይህም ከኢየሩሳሌም ጥፋት ( 70 ዓም) በኋላ ነው። የመጽሐፉ ዋና አላማ ያላመኑ ሰዎች ዳግም ልደትን እንዲያገኙ ሲሆን ያመኑት ደግሞ በእምነታቸው ውስጥ የመዳን እርግጠኝነት እንዲኖራቸው ነው። ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ከሶስቱ ወንጌላውያን በላይ ጽፏል። ከ 90% በላይ የሚሆነው የዮሐንስ ወንጌል ልዩ ሲሆን በሶስቱም ወንጌሎች ውስጥ አይገኝም። በመጽሐፉ ውስጥ ዮሐንስ ራሱን “ኢየሱስ የሚወደው,” እያለ ይጠራ ነበር።ይህም በዘመናዊ አለም ላሉ አንዳንድ ክርስቲያኖች የፈገግታ ምንጭ ሆኗል።
ስለዚህ እቅድ
በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.
More