ዘካርያስ 12:10-12
ዘካርያስ 12:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል። በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል። ምድሪቱም ታለቅሳለች፣ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣
ዘካርያስ 12:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመና መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ ወጉኝ ወደ እኔም ይመለከታሉ፤ እነርሱም ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኵር ልጅ ምርር ተብሎ እንደሚለቀስም አምርረው ያለቅሱለታል።” በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ ለሐዳድሪሞን እንደ ተለቀሰ ሁሉ በኢየሩሳሌም የሚለቀሰውም እንደዚሁ ታላቅ ልቅሶ ይሆናል። ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የየነገዱ ወንዶች ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህም ዐይነት የዳዊት ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣
ዘካርያስ 12:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፥ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፥ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል። በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደ ነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል። ምድሪቱም ታለቅሳለች፥ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥
ዘካርያስ 12:10-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው። በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም የሚሰማው ለቅሶ በመጊዶ ሜዳ ለሀዳድሪሞን እንደ ተለቀሰለት ለቅሶ ይሆናል። በምድሪቱ ላይ የእያንዳንዱ ወገን ቤተሰብ ለየራሱ ያለቅሳል፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህ ዐይነት የዳዊት ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥ የናታን ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥
ዘካርያስ 12:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል። በዚያ ቀን በመጊዶን ሜዳ እንደነበረው እንደ ሐዳድሪሞን ልቅሶ ታላቅ ልቅሶ በኢየሩሳሌም ይሆናል። ምድሪቱም ታለቅሳለች፥ እያንዳንዱ ወገን ለብቻው፥ የዳዊት ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የናታን ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥