ማሕልየ መሓልይ 2:10-12
ማሕልየ መሓልይ 2:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ልጅ ወንድሜ እንዲህ ብሎ መለሰልኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ መልካምዋ ርግቤ ሆይ፥ ነዪ። እነሆ፥ ክረምቱ ዐለፈ፥ ዝናሙም አልፎ ሄደ፤ አበባ በምድር ላይ ታየ፥ የመከርም ጊዜ ደረሰ፥ የቍርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።
Share
ማሕልየ መሓልይ 2 ያንብቡማሕልየ መሓልይ 2:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ውዴም እንዲህ አለኝ፤ “ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺ፤ አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋር ነዪ። እነሆ! ክረምቱ ዐለፈ፤ ዝናቡም አባርቶ አበቃ፤ አበቦች በምድር ላይ ታዩ፤ የዝማሬ ወቅት መጥቷል፤ የርግቦችም ድምፅ፣ በምድራችን ተሰማ።
Share
ማሕልየ መሓልይ 2 ያንብቡማሕልየ መሓልይ 2:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ፥ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ። አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቍርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።
Share
ማሕልየ መሓልይ 2 ያንብቡ