ማሕልየ መሓልይ 1:2-4
ማሕልየ መሓልይ 1:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በአፉ አሳሳም ይስመኛል፥ ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ ያማሩ ናቸው። የሽቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ሽቱ ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ። ከወደ ኋላህም ሳቡህ፥ በሽቱህ መዓዛም እንሮጣለን፤ ንጉሡ ወደ እልፍኙ አገባኝ፤ በአንቺ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ጡቶችሽን እንወዳለን፤ አንቺንም መውደድ የተገባ ነው።
Share
ማሕልየ መሓልይ 1 ያንብቡማሕልየ መሓልይ 1:2-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛልና። የሽቱህ መዐዛ ደስ ያሰኛል፤ ስምህ እንደሚፈስስ ሽቱ ነው፤ ታዲያ ቈነጃጅት ቢወድዱህ ምን ያስደንቃል! ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን፤ ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል።
Share
ማሕልየ መሓልይ 1 ያንብቡማሕልየ መሓልይ 1:2-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በአፉ መሳም ይሳመኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና። ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ። ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥ ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥ በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥ በቅንነት ይወድዱሃል።
Share
ማሕልየ መሓልይ 1 ያንብቡ