ማሕልየ መሓልይ 1:1-6
ማሕልየ መሓልይ 1:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር። በአፉ አሳሳም ይስመኛል፥ ጡቶችሽ ከወይን ይልቅ ያማሩ ናቸው። የሽቱሽ መዓዛ ከሽቱ ሁሉ መዓዛ ያማረ ነው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ሽቱ ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ። ከወደ ኋላህም ሳቡህ፥ በሽቱህ መዓዛም እንሮጣለን፤ ንጉሡ ወደ እልፍኙ አገባኝ፤ በአንቺ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ጡቶችሽን እንወዳለን፤ አንቺንም መውደድ የተገባ ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፤ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች። ፀሓይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ፤ የእናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፤ ነገር ግን የእኔን የወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ማሕልየ መሓልይ 1:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር። በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛልና። የሽቱህ መዐዛ ደስ ያሰኛል፤ ስምህ እንደሚፈስስ ሽቱ ነው፤ ታዲያ ቈነጃጅት ቢወድዱህ ምን ያስደንቃል! ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን፤ ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል። በአንተ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እንወድሳለን። አንተን እንደዚህ ማፍቀራቸው ትክክል ነው። እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እኔ ጥቍር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ ጥቍረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው። ጥቍር ስለሆንሁ ትኵር ብላችሁ አትዩኝ፤ መልኬን ያጠቈረው ፀሓይ ነውና፤ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቈጡኝ፤ የወይን ተክል ቦታዎችም ጠባቂ አደረጉኝ፤ የራሴን የወይን ተክል ቦታ ተውሁት።
ማሕልየ መሓልይ 1:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር። በአፉ መሳም ይሳመኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና። ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ። ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥ ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥ በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥ በቅንነት ይወድዱሃል። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ነገር ግን ውብ ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች። ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ማሕልየ መሓልይ 1:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከሰሎሞን መዝሙሮች መካከል በጣም ውብ የሆነው መዝሙር። ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ጣዕም ያለው ስለ ሆነ፥ ከንፈሮችህ ይሳሙኝ። የምትቀባው ሽቱ መልካም መዓዛ አለው፤ ስምህን መጥራት ሽቱን እንደ መርጨት ነው፤ ቈነጃጅትም የሚያፈቅሩህ ስለዚህ ነው። እጄን ይዘህ ሳበኝ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኙ አስገባኝ፤ በዚያም አብረን ደስ ይለናል፤ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ያስደስታል፤ ስለዚህ ቈነጃጅት ሁሉ እጅግ ያፈቅሩሃል። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ! ስሙኝ፤ እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ የመልኬ ጥቊረት እንደ ቄዳር ድንኳን ነው፤ ውበቴ ግን እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎች ነው። መልኬን ያጠቈረው የፀሐይ ቃጠሎ ነው፤ ስለዚህ ጥቊር በመሆኔ አትናቁኝ፤ የእናቴ ልጆች የሆኑ ወንድሞቼ ስለ ተጣሉኝ የወይን ተክል ጠባቂ አደረጉኝ፤ ስለዚህ የግሌ የወይን ተክል ለመጠበቅ ጊዜ አልነበረኝም።
ማሕልየ መሓልይ 1:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር። በአፉ መሳም ይሳመኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና። ዘይትህ መልካም መዓዛ አለው፥ ስምህ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፥ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ። ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥ ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥ በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥ በቅንነት ይወድዱሃል። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች። ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንኩ አትዩኝ፥ የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፥ ነገር ግን የእኔን ወይን ቦታ አልጠበቅሁም።