ሩት 4:14-22
ሩት 4:14-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሴቶችም ኑኃሚንን፦ ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፣ ስሙም በእስራኤል ይጠራ። ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት። ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው። ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት፣ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው። የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፣ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥ ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን ወለደ፥ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።
ሩት 4:14-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሴቶቹም ኑኃሚንን እንዲህ አሏት፤ “ዛሬ የሚቤዥ ቅርብ የሥጋ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፤ በመላው እስራኤልም ስሙ ይግነን። ልጁ ሕይወትሽን ያድሳታል፤ በእርጅና ዘመንሽም ይጦርሻል፤ የምትወድድሽና ከሰባት ወንዶች ልጆች የምትበልጥብሽ ምራትሽ ወልዳዋለችና።” ከዚያም ኑኃሚን ሕፃኑን ተቀብላ ታቀፈችው፤ ሞግዚትም ሆነችው። ጎረቤቶቿ የሆኑ ሴቶችም፣ “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” አሉ። ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፤ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው የእሴይ አባት ነበር። እንግዲህ የፋሬስ ቤተ ሰብ ትውልድ ይህ ነው፦ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነኦሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።
ሩት 4:14-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሴቶችም ኑኃሚንን “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ስሙም በእስራኤል ይጠራ። ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፤ በእርጅናሽም ይመገባሻል፤” አሉአት። ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፤ ሞግዚትም ሆነችው። ሴቶችም ጎረቤቶችዋ፥ “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት፤” እያሉ ስም አወጡለት፤ ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት። እርሱም የዳዊት እባት የሆነው የእሴይ አባት ነው። የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ። አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።
ሩት 4:14-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሴቶች ናዖሚን እንዲህ አሉአት፦ “ዛሬ ወራሽና ጧሪ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! እግዚአብሔር ይህን ልጅ በእስራኤል ዝነኛ ያድርገው! ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” ናዖሚም ይህን ሕፃን አቀፈችው፤ ተንከባክባም አሳደገችው። የጐረቤት ሴቶች ልጁን “ኢዮቤድ” ብለው ስም አወጡለት፤ “ለናዖሚ ወንድ ልጅ ተወለደላት!” እያሉም ለሰው ሁሉ አወሩ። የንጉሥ ዳዊት አባት የሆነውን እሴይን የወለደ ይኸው ኢዮቤድ ነው። ከፋሬስ አንሥቶ እስከ ዳዊት ያለው የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው፤ ፋሬስ ሔጽሮንን ወለደ፤ ሔጽሮን አራምን ወለደ፤ አራም ዐሚናዳብን ወለደ፤ ዐሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።
ሩት 4:14-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሴቶችም ናዖሚንን፦ “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ ጌታ ይባረክ፥ ስሙም በእስራኤል ይጠራ። ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” ናዖሚም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው። የጐረቤት ሴቶች ልጁን “ኢዮቤድ” ብለው ስም አወጡለት፤ “ለናዖሚ ወንድ ልጅ ተወለደላት!” እያሉም ለሰው ሁሉ አወሩ። የንጉሥ ዳዊት አባት የሆነውን እሴይን የወለደ ይኸው ኢዮቤድ ነው። የዳዊት የዘር ሐረግ የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፥ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥ ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን ወለደ፥ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።