የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ሩት 4:14-22

መጽሐፈ ሩት 4:14-22 መቅካእኤ

ሴቶችም ናዖሚንን፦ “ዛሬ ዋርሳ ያላሳጣሽ ጌታ ይባረክ፥ ስሙም በእስራኤል ይጠራ። ምራትሽ በጣም ትወድሻለች፤ ሰባት ልጆች ከሚያደርጉልሽ የበለጠ አድርጋልሻለች፤ አሁን ደግሞ ሕይወትሽን የሚያድስልሽና በእርጅናሽ ወራት የሚጦርሽን ወንድ ልጅ ወልዳልሻለች።” ናዖሚም ሕፃኑን ወሰደች አቀፈችውም፥ ሞግዚትም ሆነችው። የጐረቤት ሴቶች ልጁን “ኢዮቤድ” ብለው ስም አወጡለት፤ “ለናዖሚ ወንድ ልጅ ተወለደላት!” እያሉም ለሰው ሁሉ አወሩ። የንጉሥ ዳዊት አባት የሆነውን እሴይን የወለደ ይኸው ኢዮቤድ ነው። የዳዊት የዘር ሐረግ የፋሬስም ትውልድ ይህ ነው፥ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፥ ኤስሮምም አራምን ወለደ፥ አራምም አሚናዳብን ወለደ፥ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥ ሰልሞንም ቦዔዝን ወለደ፥ ቦዔዝም ኢዮቤድን ወለደ፥ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፥ እሴይም ዳዊትን ወለደ።