የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሮሜ 9:6-13

ሮሜ 9:6-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል አይ​ታ​በ​ልም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን አይ​ደ​ሉ​ምና። የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሁሉ ልጆቹ የሆ​ኑት አይ​ደ​ለም፤ ከይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃል አለው እንጂ። ልጆች እን​ዲ​ሆ​ኑት ተስፋ ያና​ገ​ረ​ለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው፤ እነ​ዚህ ከሥጋ የተ​ወ​ለዱ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች አይ​ደ​ሉም። “ከርሞ እንደ ዛሬ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ታገ​ና​ለች፤” ብሎ ተስፋ ሰጥ​ቶ​ታ​ልና። ነገር ግን ለእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ርብ​ቃም ለአ​ባ​ታ​ችን ለይ​ስ​ሐቅ መንታ በፀ​ነ​ሰች ጊዜ፥ ሳይ​ወ​ለዱ፥ ክፉና መል​ካም ሥራም ሳይ​ሠሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መም​ረጡ በምን እንደ ሆነ ይታ​ወቅ ዘንድ፥ እርሱ የጠ​ራው ነው እንጂ ሰው በሥ​ራው የሚ​መ​ረጥ አን​ዳ​ይ​ደ​ለም ያውቁ ዘንድ፥ ለር​ብቃ፥ “ታላቁ ለታ​ናሹ ይገ​ዛል” አላት። “ያዕ​ቆ​ብን ወደ​ድሁ፤ ዔሳ​ውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አ​ልና።