የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 9:6-13

ወደ ሮሜ ሰዎች 9:6-13 መቅካእኤ

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ተሽሮአል ማለት አይደለም። ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ እስራኤል አይደለምና፥ የአብርሃም ዘር ስለ ሆኑ ሁሉም የእርሱ ልጆች ናቸው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን “ዘርህ በይስሐቅ ይጠራልሃል፤” ተባለ። ይህም የሥጋ ልጆች የሆኑት የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን የተስፋው ቃል ልጆች ዘር ሆነው ይቆጠራሉ ማለት ነው። ይህም የተስፋው ቃል “በዚህ ጊዜ እመጣለሁ ሳራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤” የሚል ነውና። ይህ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ርብቃ ደግሞ ከአንድ ሰው ከአባታችን ከይስሐቅ በፀነሰች ጊዜ፥ ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ መልካም ወይም ክፉ ሳያደርጉ፥ የእግዚአብሔር የምርጫው ዓላማ እንዲጸና፥ በሥራ ሳይሆን ከጠሪው ስለሆነ፥ “ታላቁ ለታናሹ ይገዛል፤” ተብሎ ተነግሮአት ነበር። “ያዕቆብን ወደድሁ፥ ኤሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።