ሮሜ 4:9-18

ሮሜ 4:9-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ይህ ብፅዕና ለተገረዙት ብቻ ነው ወይስ ላልተገረዙትም? የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት ብለናል። ታዲያ እንዴት ተቈጠረለት? ከተገረዘ በኋላ ነው ወይስ ከመገረዙ በፊት? የተቈጠረለት ከተገረዘ በኋላ ሳይሆን ከመገረዙ በፊት ነው። ሳይገረዝ በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ፣ የመገረዝን ምልክት ይኸውም የጽድቅን ማኅተም ተቀበለ፤ ስለዚህ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙት ጽድቅ ይቈጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው። እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው፤ መገረዝ ብቻ ሳይሆን፣ አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ሁሉ ነው። እርሱ የዓለም ወራሽ እንዲሆን አብርሃምና ዘሩ ተስፋን የተቀበሉት በሕግ በኩል አልነበረም፤ ነገር ግን በእምነት ከሆነው ጽድቅ ነው። በሕግ የሚኖሩት ወራሾች ከሆኑ፣ እምነት የማይጠቅም፣ ተስፋም ከንቱ በሆነ ነበር፤ ሕግ ቍጣን ያስከትላል፤ ሕግ በሌለበት ግን መተላለፍ አይኖርም። ስለዚህ ተስፋው በእምነት መጥቷል፤ ይኸውም ተስፋው በጸጋ እንዲሆንና ለአብርሃም ዘር ሁሉ ዋስትና ይሆን ዘንድ ነው፤ ይህም በሕግ የርሱ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን፣ በእምነት የአብርሃም ለሆኑትም ነው፤ እርሱም የሁላችን አባት ነው። ይህም “የብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው፤ እርሱም ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥ፣ ያልነበረውንም እንደ ነበረ በሚያደርግ፣ ባመነበት አምላክ ፊት አባታችን ነው። “ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ ለርሱ በተነገረው መሠረት፣ ምንም ተስፋ በሌለበት፣ አብርሃም በተስፋ አምኖ የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።

ሮሜ 4:9-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ግ​ዲህ ይህ ብፅ​ዕና ስለ መገ​ዘር ተነ​ገ​ረን? ወይስ ስለ አለ​መ​ገ​ዘር? እም​ነቱ ለአ​ብ​ር​ሃም ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት እን​ላ​ለ​ንና። ለአ​ብ​ር​ሃም ጽድቅ ሆኖ የተ​ቈ​ጠ​ረ​ለት መቼ ነው? ተገ​ዝሮ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይ​ገ​ዘር? ሳይ​ገ​ዘር ነው እንጂ ተገ​ዝሮ ሳለ አይ​ደ​ለም። ሳይ​ገ​ዘር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ር​ሃ​ምን በእ​ም​ነት እንደ አጸ​ደ​ቀው በእ​ርሱ ላይ ይታ​ወቅ ዘንድ ግዝ​ረ​ትን የጽ​ድቅ ማኅ​ተም ትሆ​ነው ዘንድ ምል​ክት አድ​ርጎ ሰጠው። ሳይ​ገ​ዘሩ ለሚ​ያ​ምኑ ሁሉ አባት ሊሆን፥ አብ​ር​ሃም በእ​ም​ነት እንደ ከበረ እነ​ር​ሱም በእ​ም​ነት እን​ደ​ሚ​ከ​ብሩ ያውቁ ዘንድ ሰጠው። ለተ​ገ​ዘ​ሩ​ትም አባት ይሆን ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለተ​ገ​ዘ​ሩት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ አባ​ታ​ችን አብ​ር​ሃም ሳይ​ገ​ዘር እንደ አመነ ሳይ​ገ​ዘሩ የአ​ባ​ታ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን የሃ​ይ​ማ​ኖ​ቱን ፍለጋ ለሚ​ከ​ተሉ ደግሞ ነው እንጂ። አብ​ር​ሃም፥ ዘሩም ዓለ​ምን ይወ​ርስ ዘንድ ተስፋ ያገኘ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ሥ​ራት አይ​ደ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እር​ሱ​ንም በማ​መን በእ​ው​ነ​ተና ሃይ​ማ​ኖቱ ይህን አገኘ እንጂ። የኦ​ሪ​ትን ሕግ የፈ​ጸመ ብቻ ተስፋ የሚ​ያ​ገኝ፥ ዓለ​ም​ንም የሚ​ወ​ርስ ቢሆን ኖሮ፥ ለአ​ብ​ር​ሃም እም​ነቱ ባል​ጠ​ቀ​መ​ውም ነበር፤ ተስ​ፋ​ው​ንም ባላ​ገ​ኘም ነበር። የኦ​ሪት ሕግ በአ​ፍ​ራሹ ላይ ቅጣ​ትን ያመ​ጣ​ልና፤ የኦ​ሪት ሕግም ከሌለ መተ​ላ​ለፍ የለም። ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለዘሩ የሰ​ጠው ተስፋ የታ​መነ ይሆን ዘንድ፥ የሚ​ጸ​ድቁ በእ​ም​ነት እንጂ የኦ​ሪ​ትን ሥራ በመ​ፈ​ጸም ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ ያውቁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቅን በእ​ም​ነት አደ​ረገ። “ለብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እንደ አሉ በሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው በአ​መ​ነ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አብ​ር​ሃም የሁ​ላ​ችን አባት ነው። አብ​ር​ሃም “ዘርህ እን​ዲሁ ይሆ​ናል” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባል​ነ​በረ ጊዜ የብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት እን​ደ​ሚ​ሆን አመነ።

ሮሜ 4:9-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ይህ ብፅዕና ለተገረዙት ብቻ ነው ወይስ ላልተገረዙትም? የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት ብለናል። ታዲያ እንዴት ተቈጠረለት? ከተገረዘ በኋላ ነው ወይስ ከመገረዙ በፊት? የተቈጠረለት ከተገረዘ በኋላ ሳይሆን ከመገረዙ በፊት ነው። ሳይገረዝ በነበረው እምነት ላገኘው ጽድቅ፣ የመገረዝን ምልክት ይኸውም የጽድቅን ማኅተም ተቀበለ፤ ስለዚህ ለሚያምኑ ነገር ግን ላልተገረዙት ጽድቅ ይቈጠርላቸው ዘንድ የሁሉ አባት ነው። እርሱ ለተገረዙትም አባት ነው፤ መገረዝ ብቻ ሳይሆን፣ አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ሁሉ ነው። እርሱ የዓለም ወራሽ እንዲሆን አብርሃምና ዘሩ ተስፋን የተቀበሉት በሕግ በኩል አልነበረም፤ ነገር ግን በእምነት ከሆነው ጽድቅ ነው። በሕግ የሚኖሩት ወራሾች ከሆኑ፣ እምነት የማይጠቅም፣ ተስፋም ከንቱ በሆነ ነበር፤ ሕግ ቍጣን ያስከትላል፤ ሕግ በሌለበት ግን መተላለፍ አይኖርም። ስለዚህ ተስፋው በእምነት መጥቷል፤ ይኸውም ተስፋው በጸጋ እንዲሆንና ለአብርሃም ዘር ሁሉ ዋስትና ይሆን ዘንድ ነው፤ ይህም በሕግ የርሱ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን፣ በእምነት የአብርሃም ለሆኑትም ነው፤ እርሱም የሁላችን አባት ነው። ይህም “የብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው፤ እርሱም ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥ፣ ያልነበረውንም እንደ ነበረ በሚያደርግ፣ ባመነበት አምላክ ፊት አባታችን ነው። “ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ ለርሱ በተነገረው መሠረት፣ ምንም ተስፋ በሌለበት፣ አብርሃም በተስፋ አምኖ የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።

ሮሜ 4:9-18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንግዲህ ይህ ብፅዕና ስለ መገረዝ ተነገረ? ወይስ ደግሞ ስለ አለመገረዝ? እምነቱ ለአብርሃም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት እንላለንና። እንዴት ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ተገርዞስ አይደለም፥ ሳይገረዝ ነበር እንጂ። ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው፥ ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው። የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም። ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤ ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም። ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው። ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ።

ሮሜ 4:9-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ታዲያ፥ ዳዊት የተናገረው ይህ በረከት ለተገረዙት ብቻ ነውን? ወይስ ላልተገረዙትም? ላልተገረዙትም ነው፤ “አብርሃም በእግዚአብሔር ስላመነ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ብለናል። እንግዲህ አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት መቼ ነው? ከመገረዙ በፊት ነውን ወይስ ከተገረዘ በኋላ? ከመገረዙ በፊት ነው እንጂ ከተገረዘ በኋላ አይደለም። አብርሃም ገና ከመገረዙ በፊት እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደ ተቈጠረለት ማረጋገጫ ምልክት እንዲሆነው ተገረዘ፤ ስለዚህ አብርሃም፥ ሳይገረዙ ለሚያምኑና እምነታቸው ጽድቅ ሆኖ ለሚቈጠርላቸው ሁሉ አባት ነው። እንዲሁም አብርሃም ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት አባት የሆነበትም ምክንያት በመገረዛቸው ብቻ ሳይሆን እርሱ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት በመከተላቸውም ጭምር ነው። ለአብርሃምና ለዘሩ ዓለምን እንደሚወርስ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠው በእምነት ስላገኘው ጽድቅ ነው እንጂ ሕግን በመፈጸሙ አይደለም። የተስፋው ወራሾች ሕግን የሚፈጽሙ ሰዎች ከሆኑማ እምነት ዋጋ አይኖረውም፤ ተስፋም ከንቱ መሆኑ ነው። ሕግ የሚያመጣው የእግዚአብሔርን ቊጣ ነው፤ ሕግ ከሌለ ግን ሕግን የመተላለፍ በደል አይኖርም። ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና። ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር። አብርሃም ዘርህ እጅግ ይበዛል ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ሕዝብ አባት እንደሚሆን ያመነውና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ በማይጣልበት ነገር ነው።

ሮሜ 4:9-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እንግዲህ ይህ መባረክ በመገረዝ መጣን? ወይስ ደግሞ ባለመገረዝ? አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት እንላለንና። እንዴት ታዲያ ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ሳይገረዝ ነበር እንጂ፤ ከተገረዘ በኋላ አይደለም። ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤ ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ጭምር ነው። ዓለምን እንዲወርስ ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም። ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል፤ የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤ ሕጉ መቅሠፍትን ያስከትላልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም። ስለዚህ በእምነት የሆነው፥ ተስፋው በእምነት እንዲያርፍና ለዘሩ ሁሉ እንዲሆን ነው፥ ይህም ሕግ ፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአብርሃምን እምነት የሚጋሩትንም ጭምር ነው፥ እርሱ የሁላችንም አባት ነውና፥ “የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ የሞተውን ሕያው በሚያደርግ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት አምላክ ፊት ነው። “ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ እንደ ተነገረው፥ ተስፋ በሌለበት የብዙ ሕዝቦች አባት እንደሚሆን በተስፋ አመነ።