የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሮሜ 4:17-25

ሮሜ 4:17-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ለብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እንደ አሉ በሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው በአ​መ​ነ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አብ​ር​ሃም የሁ​ላ​ችን አባት ነው። አብ​ር​ሃም “ዘርህ እን​ዲሁ ይሆ​ናል” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባል​ነ​በረ ጊዜ የብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት እን​ደ​ሚ​ሆን አመነ። አብ​ር​ሃም የመቶ ዓመት ሽማ​ግሌ ስለ​ሆነ እንደ ምውት የሆ​ነ​ውን የራ​ሱን ሥጋና የሣራ ማኅ​ፀን ምውት መሆ​ኑን እያየ በእ​ም​ነት አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያና​ገ​ረ​ለ​ት​ንም ተስፋ ይቀ​ራል ብሎ አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም፤ በእ​ም​ነት ጸና እንጂ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን ሰጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ሊያ​ደ​ር​ግ​ለት እን​ደ​ሚ​ችል በፍ​ጹም ልቡ አመነ። ስለ​ዚ​ህም ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት። ነገር ግን “ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት” የሚ​ለው ቃል የተ​ጻፈ ስለ እርሱ ብቻ አይ​ደ​ለም። ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን፥ ሊያ​ስ​ነ​ሣ​ንና ሊያ​ጸ​ድ​ቀን የተ​ነ​ሣ​ውን ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው ስለ​ም​ና​ምን ስለ እናም ነው እንጂ።

ሮሜ 4:17-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ይህም “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው፤ እርሱም ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥ፣ ያልነበረውንም እንደ ነበረ በሚያደርግ፣ ባመነበት አምላክ ፊት አባታችን ነው። “ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ ለእርሱ በተነገረው መሠረት፣ ምንም ተስፋ በሌለበት፣ አብርሃም በተስፋ አምኖ የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ። እርሱ የመቶ ዓመት ሰው ሆኖ ሳለ፣ የራሱም ሰውነት ሆነ የሣራ ማሕፀን ምዉት እንደ ነበረ እያወቀ በእምነቱ አልደከመም። ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም፤ እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ እንደሚፈጽም በሙሉ ልብ ርግጠኛ ነበር። ስለዚህ፣ “ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት።” “ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው ቃል የተጻፈው ለእርሱ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ ለሚቈጥርልን፣ ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በእርሱ ለምናምን ለእኛም ጭምር ነው። እርሱ ስለ ኀጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ።

ሮሜ 4:16-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው። ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ። የመቶ ዓመትም ሽማግሌ ስለ ሆነ እንደ ምውት የሆነውን የራሱን ሥጋና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ፤ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም። ስለዚህ ደግሞ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ነገር ግን፦ ተቍኦጠረለት የሚለው ቃል ስለ እርሱ ብቻ የተጻፈ አይደለም፥ ስለ እኛም ነው እንጂ፤ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታንችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቍኦጠርልን ዘንድ አለው።

ሮሜ 4:17-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር። አብርሃም ዘርህ እጅግ ይበዛል ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ሕዝብ አባት እንደሚሆን ያመነውና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ በማይጣልበት ነገር ነው። ዕድሜው መቶ ዓመት ያኽል ስለ ነበረ በሥጋው መድከም እንደ ሞተ በመሆን ምክንያት መውለድ እንደማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆንዋ መውለድ እንደማትችል ቢያውቅም በእምነቱ ደካማ አልሆነም። በእምነቱ ብርቱ ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብር ሰጠ እንጂ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ባለማመን ከቶ አልተጠራጠረም። እግዚአብሔር የሰጠውንም ተስፋ የሚፈጽም መሆኑን በሙሉ ልብ ያምን ነበር። ስለዚህ ነው ለአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት። ነገር ግን “ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው ቃል የተጻፈው ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን ለእኛም ጭምር ነው፤ ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ባስነሣው አምላክ ለምናምን ለእኛም እምነታችን ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርልናል። ይህ ጌታችን ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ የተሰጠውና እኛንም ለማጽደቅ ከሞት የተነሣው ነው።