የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ሮሜ ሰዎች 4:17-25

ወደ ሮሜ ሰዎች 4:17-25 አማ2000

“ለብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እንደ አሉ በሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው በአ​መ​ነ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አብ​ር​ሃም የሁ​ላ​ችን አባት ነው። አብ​ር​ሃም “ዘርህ እን​ዲሁ ይሆ​ናል” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባል​ነ​በረ ጊዜ የብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት እን​ደ​ሚ​ሆን አመነ። አብ​ር​ሃም የመቶ ዓመት ሽማ​ግሌ ስለ​ሆነ እንደ ምውት የሆ​ነ​ውን የራ​ሱን ሥጋና የሣራ ማኅ​ፀን ምውት መሆ​ኑን እያየ በእ​ም​ነት አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያና​ገ​ረ​ለ​ት​ንም ተስፋ ይቀ​ራል ብሎ አል​ተ​ጠ​ራ​ጠ​ረም፤ በእ​ም​ነት ጸና እንጂ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን ሰጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ሊያ​ደ​ር​ግ​ለት እን​ደ​ሚ​ችል በፍ​ጹም ልቡ አመነ። ስለ​ዚ​ህም ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት። ነገር ግን “ጽድቅ ሆኖ ተቈ​ጠ​ረ​ለት” የሚ​ለው ቃል የተ​ጻፈ ስለ እርሱ ብቻ አይ​ደ​ለም። ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን፥ ሊያ​ስ​ነ​ሣ​ንና ሊያ​ጸ​ድ​ቀን የተ​ነ​ሣ​ውን ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው ስለ​ም​ና​ምን ስለ እናም ነው እንጂ።