ራእይ 16:8-21
ራእይ 16:8-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አራተኛው መልአክ ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሐይም ሰዎችን በግለትዋ ለማቃጠል ኀይል ተሰጣት፤ ሰዎች በታላቅ ግለት ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ንስሓ አልገቡም፤ እርሱንም አላከበሩም። አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት ጨለማ ሆነ፤ ሰዎች ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤ ከሕመማቸውና ከቊስላቸው የተነሣ የሰማይን አምላክ ተራገሙ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም። ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ። ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ፥ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጉንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ። እነርሱ ተአምራት የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ እነዚህ መናፍስት ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት ሰዎችን ለመሰብሰብ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይሄዳሉ። “እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!” መናፍስቱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቡአቸው። ሰባተኛው መልአክ ጽዋውን በዐየር ላይ አፈሰሰ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው ዙፋን “ተፈጸመ!” የሚል ከፍተኛ ድምፅ ወጣ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ይህን የመሰለ ታላቅ የምድር መናወጥ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ ሆኖ አያውቅም። ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት። ደሴቶች ሁሉ ወዲያ ሸሹ፤ ተራራዎችም አልተገኙም፤ እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን በረዶ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበረ ሰዎች በበረዶው መቅሠፍት ምክንያት እግዚአብሔርን ተሳደቡ።
ራእይ 16:8-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት። ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም። አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች፤ ከስቃይም የተነሣ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፤ ከስቃያቸውና ከቍስላቸውም የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም። ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ። ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤ ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ። “እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ “ተፈጽሞአል!” የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ። መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ። ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች። ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ፤ ተራራዎችም አልተገኙም። በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።
ራእይ 16:8-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሓይም ሰዎችን በእሳት እንድታቃጥል ኀይል ተሰጣት። እነርሱም በታላቅ ሐሩር ተቃጠሉ፤ በእነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሓ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም። ዐምስተኛውም መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ፤ ሰዎችም ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤ ደግሞም ከሥቃያቸውና ከቍስላቸው የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ እንጂ ከሥራቸው ንስሓ አልገቡም። ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸው የወንዙ ውሃ ደረቀ። ከዚያም ከዘንዶው አፍ፣ ከአውሬው አፍና ከሐሰተኛው ነቢይ አፍ እንቍራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ። እነርሱም ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲሰበስቧቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይሄዳሉ። “እነሆ፤ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ዕራቍቱን እንዳይሆን ኀፍረቱም እንዳይታይ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።” እነርሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው። ሰባተኛውም መልአክ ጽዋውን በአየር ላይ አፈሰሰ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው ዙፋንም “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ወጣ። ከዚያም መብረቅ፣ ድምፅ፣ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ የምድር መናወጥ ታይቶ አይታወቅም፤ ነውጡም እጅግ ታላቅ ነበር። ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔርም ታላቂቱን ባቢሎን አስታወሰ፤ በብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የተሞላውን ጽዋ ሰጣት። ደሴቶች ሁሉ ሸሹ፤ ተራሮችም ሊገኙ አልቻሉም። በሚዛን ሲመዘን እያንዳንዱ አርባ ዐምስት ኪሎ ግራም የሚሆን ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ።
ራእይ 16:8-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት። ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፥ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፥ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሐ አልገቡም። አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች ከስቃይም የተነሳ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፥ ከስቃያቸውና ከቍስላቸውም የተነሳ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፥ ከስራቸውም ንስሐ አልገቡም። ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ። ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤ ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ። እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው። በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ፦ ተፈጽሞአል የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ። መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ። ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች። ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም። በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሳ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፥ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።
ራእይ 16:8-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አራተኛው መልአክ ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሐይም ሰዎችን በግለትዋ ለማቃጠል ኀይል ተሰጣት፤ ሰዎች በታላቅ ግለት ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ንስሓ አልገቡም፤ እርሱንም አላከበሩም። አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት ጨለማ ሆነ፤ ሰዎች ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤ ከሕመማቸውና ከቊስላቸው የተነሣ የሰማይን አምላክ ተራገሙ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም። ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ። ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ፥ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጉንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ። እነርሱ ተአምራት የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ እነዚህ መናፍስት ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት ሰዎችን ለመሰብሰብ ወደ ዓለም ነገሥታት ሁሉ ይሄዳሉ። “እነሆ! እኔ እንደ ሌባ በድንገት እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይሆንና ኀፍረቱን ሰዎች እንዳያዩበት ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው የተመሰገነ ነው!” መናፍስቱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቡአቸው። ሰባተኛው መልአክ ጽዋውን በዐየር ላይ አፈሰሰ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው ዙፋን “ተፈጸመ!” የሚል ከፍተኛ ድምፅ ወጣ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ይህን የመሰለ ታላቅ የምድር መናወጥ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ ሆኖ አያውቅም። ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔር ታላቂቱን ባቢሎንን አስታወሰ፤ የብርቱ ቊጣው ወይን ጠጅ የተሞላበትን ጽዋ እንድትጠጣም አደረጋት። ደሴቶች ሁሉ ወዲያ ሸሹ፤ ተራራዎችም አልተገኙም፤ እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን በረዶ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበረ ሰዎች በበረዶው መቅሠፍት ምክንያት እግዚአብሔርን ተሳደቡ።
ራእይ 16:8-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት እንድታቃጥል ሥልጣን ተሰጣት። ሰዎችም በታላቅ ትኩሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም። አምስተኛውም መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች፤ ከስቃይም የተነሣ ሰዎች መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፤ ከስቃያቸውና ከቁስላቸውም የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም። ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውሃው ደረቀ። ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ፥ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጉንቸሮችን የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ ምልክት እያደረጉ፥ በታላቁና ሁሉን በሚገዛው በእግዚአብሔር ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ። “እነሆ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።” በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው። ሰባተኛውም መልአክ ጽዋውን በአየር ላይ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ። መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፤ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ነውጡ እጅግ ትልቅ ነበር። ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች። ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ፤ ተራራዎችም አልተገኙም። በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነበርና።