መዝሙር 88:1-18

መዝሙር 88:1-18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ። ጽድ​ቅ​ህ​ንም በአፌ ለልጅ ልጅ እና​ገ​ራ​ለሁ። “ምሕ​ረ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አን​ጻ​ለሁ” ብለ​ሃ​ልና፥ ጽድ​ቅህ በሰ​ማይ ጸና። ከመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ለባ​ሪ​ያ​ዬም ለዳ​ዊት ማልሁ፥ ዘር​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ፥ ዙፋ​ን​ህ​ንም ለልጅ ልጅ አጸ​ና​ለሁ። አቤቱ፥ ሰማ​ያት ክብ​ር​ህን ጽድ​ቅ​ህ​ንም ደግሞ በቅ​ዱ​ሳን ማኅ​በር ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደ​መ​ናት ማን ይተ​ካ​ከ​ለ​ዋል? ከአ​ማ​ል​ክ​ትስ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማን ይመ​ስ​ለ​ዋል? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቅ​ዱ​ሳን ምክር ክቡር ነው፤ በዙ​ሪ​ያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላ​ቅና ግሩም ነው። አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እው​ነ​ትም ይከ​ብ​ብ​ሃል። የባ​ሕ​ርን ኀይል አንተ ትገ​ዛ​ለህ፥ የሞ​ገ​ዱ​ንም መና​ወጥ አንተ ዝም ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ። አንተ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን እንደ ተገ​ደለ አዋ​ረ​ድ​ኸው፥ በኀ​ይ​ል​ህም ክንድ ጠላ​ቶ​ች​ህን በተ​ን​ሃ​ቸው። ሰማ​ያት የአ​ንተ ናቸው፥ ምድ​ርም የአ​ንተ ናት፤ ዓለ​ምን በሙሉ አንተ መሠ​ረ​ትህ። ባሕ​ር​ንና መስ​ዕን አንተ ፈጠ​ርህ፤ ታቦ​ርና አር​ሞ​ን​ኤም በስ​ምህ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ስም​ህ​ንም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። ክን​ድህ ከኀ​ይ​ልህ ጋር ነው፤ እጅህ በረ​ታች፥ ቀኝ​ህም ከፍ ከፍ አለች። የዙ​ፋ​ንህ መሠ​ረት ፍት​ሕና ርትዕ ነው፤ ምሕ​ረ​ትና እው​ነት በፊ​ትህ ይሄ​ዳሉ። እል​ል​ታን የሚ​ያ​ውቅ ሕዝብ ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ በፊ​ትህ ብር​ሃን ይሄ​ዳሉ። በስ​ምህ ቀኑን ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ከፍ ከፍ ይላሉ፤ የኀ​ይ​ላ​ቸው ትም​ክ​ሕት አንተ ነህና፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ህም ቀን​ዳ​ችን ከፍ ከፍ ይላ​ልና። ረድ​ኤ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። ንጉ​ሣ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነውና።

መዝሙር 88:1-18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ። ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል። ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ተቃርባለች። ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋራ ተቈጠርሁ፤ ዐቅምም ዐጣሁ። በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣ ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣ አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣ ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ። በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤ በጨለማ ጕድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ። የቍጣህ ክብደት በላዬ ዐርፏል፤ በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል። ሴላ የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤ እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤ ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤ ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ። ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን? የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣ ታማኝነትህስ እንጦርጦስ ይነገራልን? ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣ ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን? እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ? እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤ መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ። ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤ መዓትህም አጠፋኝ። ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ በአንድነትም ዙሪያዬን ዐጥረው ያዙኝ። ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።

መዝሙር 88:1-18 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አዳኜ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ትረዳኝ ዘንድ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ሌሊቱንም በአንተ ፊት አለቅሳለሁ። እባክህ ጸሎቴን ስማ! ጩኸቴንም አድምጥ! ብዙ መከራ ስለ ደረሰብኝ ለመሞት ተቃርቤአለሁ። ሞተው ወደ መቃብር ከሚወርዱት ሰዎች ጋር ተቈጥሬአለሁ፤ ምንም ረዳት እንደሌለው ሰው ሆኜአለሁ። በሙታን መካከል ፈጽሞ እንደ ተተዉ፥ ተገድለው በመቃብር እንደ ተጋደሙ፥ ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና የአንተ እንክብካቤ ከእነርሱ እንደ ተቋረጠ ሰዎች መስዬአለሁ። አንተ ወደ መቃብር አዘቅት ወደ ጨለመውና ጥልቅ ወደ ሆነው ጒድጓድ አወረድከኝ። ቊጣህ እጅግ ከብዶኛል፤ የቊጣህም ማዕበል አጥለቅልቆኛል። ወዳጆቼ ሁሉ ከእኔ እንዲርቁ አደረግህ፤ በፊታቸውም አጸያፊ አደረግኸኝ፤ ዙሪያዬ ታጥሮአል፤ ማምለጫም የለኝም። ሐዘኔ ከመብዛቱ የተነሣ ዐይኖቼ ደከሙ፤ እግዚአብሔር ሆይ! በየቀኑ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እጆቼንም ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ። ለሙታን ተአምራትን ታደርጋለህን? እነርሱስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ዘለዓለማዊ ፍቅርህ በመቃብር፥ ታማኝነትህ በጥፋት ቦታ ይነገራልን? ተአምራትህ በጨለማ ስፍራ ይታወቃሉን? ታዳጊነትህስ በተረሱ ሰዎች አገር ይታያልን? እግዚአብሔር ሆይ! እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በየማለዳውም ወደ አንተ እጸልያለሁ። እግዚአብሔር ሆይ! ለምን ትጥለኛለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ? ከልጅነቴ ጀምሮ ጭንቀት ደርሶብኝ እስከ ሞት ተቃርቤአለሁ፤ ከማስደንገጥህ የተነሣ ተስፋ ቈርጬአለሁ። ብርቱ ቊጣህ አደቀቀኝ፤ አስፈሪው ቅጣትህ ያጠፋኛል። እነርሱ ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤ ፈጽመውም አሰጠሙኝ። የቅርብ ወዳጆቼንና ጓደኞቼን ከእኔ አርቀህ ጨለማ ብቻ ከእኔ ጋር እንዲቀር አደረግህ።

መዝሙር 88:1-18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አቤቱ፥ የመድኃኒቴ አምላክ፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፥ ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለችና። ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ። ለዘለዓለም እንደማታስባቸው፥ እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ በሙታን ውስጥ እንዳሉ የተጣልሁ ሆንሁ፥ እነርሱም ከእጅህ ተለዩ። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ። በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ። የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥ በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥ ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም። ዐይኖቼም በመከራ ፈዘዙ፥ አቤቱ፥ ሁልጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ። በውኑ ለሙታን ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህን? ጥላዎችስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? በመቃብርስ ውስጥ ጽኑ ፍቅርህን፥ እውነትህንስ በጥፋት ስፍራ ይነገራሉን? ድንቅ ሥራህ በጨለማ፥ ጽድቅህም በሚረሳበት ምድር ትታወቃለችን? አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች። አቤቱ፥ ነፍሴን ለምን ትጥላለህ? ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ? እኔ ከታናሽነቴ ችግረኛ ለሞትም የቀረብሁ ነኝ፥ በአስደንጋጭ ነገሮችህ ተሰቃየሁ፤ ምንም አቅም የለኝም። ቁጣህ በላዬ አለፈ፥ አስፈሪ ድርጊቶችህ አደቀቁኝ። ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድ ላይም አጥለቀለቁኝ።