መዝሙር 87:5-7
መዝሙር 87:5-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በርግጥም ስለ ጽዮን፣ “ይህም ያም ሰው በርሷ ውስጥ ተወለዱ፤ ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣ “ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣ “ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።
Share
መዝሙር 87 ያንብቡመዝሙር 87:5-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ልዑል እግዚአብሔር ራሱ ስለሚመሠርታት ስለ ጽዮን፦ “ይህም ሕዝብ፥ ያም ሕዝብ በእርስዋ ውስጥ ተወልደዋል” ይባላል። እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሁሉ ይመዘግባል፤ እያንዳንዱንም “በጽዮን የተወለደ” ብሎ ይጠራዋል። ዘማሪዎችና ጨፋሪዎች “የበረከታችን ሁሉ መገኛ ጽዮን ናት” እያሉ በደስታ ይዘምራሉ።
Share
መዝሙር 87 ያንብቡመዝሙር 87:5-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘለዓለም እንደማታስባቸው በሙታን መካከል የተጣልሁ ሆንሁ፤ እነርሱ ከእጅህ ርቀዋልና። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጕድጓድ አስቀመጡኝ። በእኔ ላይ ቍጣህ ጸና፥ መቅሠፍትህን ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።
Share
መዝሙር 87 ያንብቡመዝሙር 87:5-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በርግጥም ስለ ጽዮን፣ “ይህም ያም ሰው በርሷ ውስጥ ተወለዱ፤ ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣ “ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣ “ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።
Share
መዝሙር 87 ያንብቡ