መዝሙር 62:5-8
መዝሙር 62:5-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ደስተኞች ከንፈሮቼም ስምህን ያመሰግናሉ። በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም እናገርልሃለሁ፤ ረዳቴ ሆነኽልኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ እታመናለሁ። ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ።
Share
መዝሙር 62 ያንብቡመዝሙር 62:5-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ነውና። ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም። መዳኔና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ ብርቱ ዐለቴና መሸሸጊያዬ በእግዚአብሔር ነው። ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ
Share
መዝሙር 62 ያንብቡ