የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 46:1-11

መዝሙር 46:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣ ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም። ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ተራሮችም ከውሆቹ ሙላት የተነሣ ቢንቀጠቀጡም አንደናገጥም። ሴላ የእግዚአብሔርን ከተማ፣ የልዑልን የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኙ የወንዝ ፈሳሾች አሉ። እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤ አምላክ በማለዳ ይረዳታል። ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች። የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ ኑና የእግዚአብሔርን ሥራ፣ ምድርንም እንዴት ባድማ እንዳደረጋት እዩ። ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤ ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል። “ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።” የሰራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ

መዝሙር 46:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው። ስለዚህ ምድር ብትናወጥ፥ ተራራዎች ወደ ጥልቅ ባሕር ቢወድቁ፥ ባሕሮች ታውከው ድምፃቸውን ቢያሰሙ፥ በእነርሱም የእንቅስቃሴ ኀይል ተራራዎች ቢንቀጠቀጡ አንፈራም። ጅረቶችዋ የልዑል እግዚአብሔርን ቅዱስ ማደሪያ፥ የአምላክን ከተማ የሚያስደስቱ አንዲት ወንዝ አለች። እግዚአብሔር ከእርስዋ ጋር ስለ ሆነ ያቺ ከተማ አትናወጥም፤ ጠዋት በማለዳ እግዚአብሔር ይረዳታል። ሕዝቦች ተሸበሩ፤ ነገሥታትም ወደቁ፤ እግዚአብሔር ድምፁን ባሰማ ጊዜ ምድር ቀለጠች። የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን ሥራ እዩ፤ በምድር ላይ ያመጣውን ጥፋት ተመልከቱ። እርሱ በመላው ዓለም የሚካሄደውን ጦርነት ሁሉ ያቆማል፤ ቀስትንና ጦርን ይሰብራል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል። ጸጥ ብላችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ዕወቁ፤ በሕዝቦች መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ። የሠራዊት አምላክ ከእኛ ጋር ነው፤ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።

መዝሙር 46:1-11

መዝሙር 46:1-11 NASVመዝሙር 46:1-11 NASVመዝሙር 46:1-11 NASV