መዝሙረ ዳዊት 46
46
1ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ምሥጢር፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2 #
መዝ. 48፥4፤ ኢሳ. 33፥2። አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥
ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።
3ስለዚህ ምድር ብትለዋወጥ፥
ተራሮችም በባሕር ልብ ውስጥ ቢናወጡ አንፈራም።
4 #
መዝ. 93፥3-4፤ ኢዮብ 9፥5-6፤ ኢሳ. 24፥18-20፤ 54፥10። ውኆቻቸው እየገነፈሉ ጮኹ፥
ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተንቀጠቀጡ።
5 #
መዝ. 48፥2-3፤ 76፥3። የወንዝ ፈሳሾች የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛሉ፥
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ።
6 #
ኢሳ. 7፥14። እግዚአሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፥
እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል።
7 #
መዝ. 2፥1-5፤ 48፥5-8፤ 76፥7-9፤ ኢሳ. 17፥12-14። አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥
እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።
8የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
9 #
መዝ. 48፥9-10። የጌታን ሥራ፥
በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።
10 #
መዝ. 76፥4። እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ያስቆማል፥
ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቆራርጣል፥
በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።
11 #
መዝ. 48፥11። ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥
በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥
በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።
12የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥
የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 46: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ