መዝሙር 45:10-17
መዝሙር 45:10-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ልጄ ሆይ፤ ስሚ፤ አስተውዪ፤ ጆሮሽንም አዘንብዪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። ንጉሥ በውበትሽ ተማርኳል፤ ጌታሽ ነውና አክብሪው። የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል። የንጉሥ ልጅ ከላይ እስከ ታች ተሸልማ እልፍኟ ውስጥ አለች፤ ልብሷም ወርቀ ዘቦ ነው። በጥልፍ ሥራ ባጌጠ ልብስ ወደ ንጉሥ ትወሰዳለች፤ ደናግል ጓደኞቿም ተከትለዋት፣ ወደ አንተ ይመጣሉ። በደስታና በሐሤት ወደ ውስጥ ይመሯቸዋል፤ ወደ ንጉሡም ቤተ መንግሥት ይገባሉ። ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ፤ ገዦችም አድርገሽ በምድር ሁሉ ትሾሚያቸዋለሽ። ስምሽን በትውልድ ሁሉ ዘንድ መታሰቢያ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ያወድሱሃል።
መዝሙር 45:10-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አንቺ ልጄ ሆይ! የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤ ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው። የጢሮስ ሰዎች ስጦታ ያመጡልሻል፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል። በቤተ መንግሥት የተቀመጠችው ልዕልት አጊጣለች ልብስዋም በወርቅ አሸብርቆአል። ጌጠኛ ልብስዋንም ተጐናጽፋ ወደ ንጉሡ ትቀርባለች፤ ሚዜዎችዋ የሆኑ ልጃገረዶችም ያጅቡአታል፤ በደስታና በሐሤትም አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ። ንጉሥ ሆይ! በቀድሞ አባቶችህ ተተክተው የሚነግሡ ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤ አንተም በምድር ሁሉ ላይ ልዑላን አድርገህ ትሾማቸዋለህ። እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
መዝሙር 45:10-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፥ በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች። ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፥ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፥ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና እጅ ንሺው። የጢሮስ ሴት ልጅ፥ የምድር ባለ ጠጎች አሕዛብ በፊትሽ ደጅ ይጠናሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው፥ ልብስዋ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው። በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፥ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፥ በደስታና በሐሴት ይወስዱአቸዋል፥ ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል። በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ።