አንቺ ልጄ ሆይ! የምልሽን ስሚ፤ ቃሌንም አድምጪ፤ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ። በውበትሽ ንጉሡ ይወድሻል፤ ሆኖም ጌታሽ በመሆኑ እጅ በመንሣት አክብሪው። የጢሮስ ሰዎች ስጦታ ያመጡልሻል፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል። በቤተ መንግሥት የተቀመጠችው ልዕልት አጊጣለች ልብስዋም በወርቅ አሸብርቆአል። ጌጠኛ ልብስዋንም ተጐናጽፋ ወደ ንጉሡ ትቀርባለች፤ ሚዜዎችዋ የሆኑ ልጃገረዶችም ያጅቡአታል፤ በደስታና በሐሤትም አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ። ንጉሥ ሆይ! በቀድሞ አባቶችህ ተተክተው የሚነግሡ ብዙ ልጆች ይኖሩሃል፤ አንተም በምድር ሁሉ ላይ ልዑላን አድርገህ ትሾማቸዋለህ። እኔ በየትውልዱ ዝናህን እገልጣለሁ፤ ስለዚህ ሕዝቦች ሁሉ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያመሰግኑሃል።
መጽሐፈ መዝሙር 45 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 45:10-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos