መዝሙር 3:3-5
መዝሙር 3:3-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ። ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 3 ያንብቡመዝሙር 3:3-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፤ ክብሬና ራሴን ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ። በቃሌ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ ከተቀደሰ ተራራውም ሰማኝ። እኔ ተኛሁ፤ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔርም አንሥቶኛልና ተነሣሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 3 ያንብቡመዝሙር 3:3-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ። ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 3 ያንብቡመዝሙር 3:3-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ጋሻዬ ነህ፤ ድልን በማጐናጸፍ ክብርን የምትሰጠኝ አንተ ነህ። ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ እርሱም በተቀደሰ ተራራው ላይ ሆኖ ይሰማኛል። እኔ ተኛሁ፥ አንቀላፋሁም፤ እግዚአብሔር ሌሊቱን ሙሉ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ።
ያጋሩ
መዝሙር 3 ያንብቡ