መዝሙር 28:6-9
መዝሙር 28:6-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንደ ሊባኖስ ላም ያከሳዋል። ተወዳጅ ግን አንድ ቀንድ እንዳለው ርኤም ልጅ ነው። የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል። የእግዚአብሔር ቃል ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። የእግዚአብሔር ቃል ዋሊያዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ዛፎችንም ይገልጣል፤ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
ያጋሩ
መዝሙር 28 ያንብቡመዝሙር 28:6-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የልመናዬን ቃል ሰምቷልና፣ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን። እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው። ሕዝብህን አድን፤ ርስትህንም ባርክ፤ እረኛ ሁናቸው፤ ለዘላለሙም ዐቅፈህ ያዛቸው።
ያጋሩ
መዝሙር 28 ያንብቡመዝሙር 28:6-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የልመናዬን ድምፅ ስለ ሰማኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። እግዚአብሔር ኀይሌና ጋሻዬ ነው፤ ስለሚረዳኝና ደስ ስለሚያሰኘኝም በእርሱ እተማመናለሁ፤ በመዝሙሮቼም አመሰግነዋለሁ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፤ ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥም የመዳኛ ከለላው ነው። አምላክ ሆይ! ሕዝብህን አድን፤ የአንተ የሆኑትንም ባርክ፤ እረኛቸውም ሁን፤ ለዘለዓለምም ተንከባከባቸው።
ያጋሩ
መዝሙር 28 ያንብቡ