መዝሙር 25:16-22
መዝሙር 25:16-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣ ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ። የልቤ መከራ በዝቷል፤ ከጭንቀቴ ገላግለኝ። ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤ ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ። ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤ እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ። ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤ መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ። አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ። አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
Share
መዝሙር 25 ያንብቡመዝሙር 25:16-22 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እኔ ብቸኛና ችግረኛ ስለ ሆንኩ አምላክ ሆይ! ወደ እኔ ተመለስ፤ በጎነትንም አድርግልኝ። ከደረሰብኝ ችግር ሁሉ እንድላቀቅ አድርገኝ፤ ከጭንቀቴም ሁሉ አድነኝ። ችግሬንና ሥቃዬን ተመልከት፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በልልኝ። ጠላቶቼ ምን ያኽል እንደ በዙ እይ፤ ምን ያኽል እንደ ጠሉኝም ተመልከት። ጠብቀኝ፤ አድነኝም፤ አንተን መጠጊያ ስላደረግሁ ኀፍረት እንዲደርስብኝ አታድርግ። አምላክ ሆይ! አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ቅንነትና ቀጥተኛነት እንዲጠብቁኝ አድርግ። አምላክ ሆይ! እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድን!
Share
መዝሙር 25 ያንብቡ