መዝሙር 19:7-8
መዝሙር 19:7-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እነዚያ በፈረሶችና በሰረገላዎች ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን። እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
ያጋሩ
መዝሙር 19 ያንብቡመዝሙር 19:7-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤ አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ዐይንን ያበራል።
ያጋሩ
መዝሙር 19 ያንብቡመዝሙር 19:7-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል። የእግዚአብሔር ሕግ ትክክል ነው፤ ለልብ ደስታን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ለዐይን ብርሃንን ይሰጣል።
ያጋሩ
መዝሙር 19 ያንብቡ