መዝሙር 15:2-5
መዝሙር 15:2-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ በጎነቴን አትሻትምና። ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳን ላይ ተገለጠ። ደዌያቸው በዛ፤ ከዚያም በኋላ ተፋጠኑ፤ በደም ማኅበራቸው አልተባበርም። ስማቸውንም በአፌ አልጠራም። እግዚአብሔር የርስቴ ዕድል ፋንታና ጽዋዬ ነው፥ ርስቴን የምትመልስ አንተ ነህ።
ያጋሩ
መዝሙር 15 ያንብቡመዝሙር 15:2-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አካሄዱ የቀና፣ ጽድቅን የሚያደርግ፤ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤ በምላሱ የማይሸነግል፤ በባልንጀራው ላይ ክፉ የማይሠራ፤ ወዳጁን የማያማ፤ ነውረኛ በፊቱ የተናቀ፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ግን የሚያከብር፤ ዋጋ የሚያስከፍለውም ቢሆን፣ ቃለ መሐላውን የሚጠብቅ፤ ገንዘቡን በዐራጣ የማያበድር፣ በንጹሓን ላይ ጕቦ የማይቀበል።
ያጋሩ
መዝሙር 15 ያንብቡመዝሙር 15:2-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርሱ ነቀፋ የሌለበት ሕይወትን የሚኖርና ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ፥ ከልቡም እውነትን የሚናገር፥ ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥ በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥ ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥ ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥ ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥ ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
ያጋሩ
መዝሙር 15 ያንብቡ