መዝሙረ ዳዊት 15
15
1የዳዊት መዝሙር።
#
ኢሳ. 56፥7። አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል?
በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
2 #
መዝ. 119፥1። በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥
በልቡም እውነትን የሚናገር።
3በአንደበቱ የማይሸነግል፥
በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥
የሚቀርቡትን የማይሰድብ።
4ኃጢአተኛ ሰው በፊቱ የተናቀ፥
ጌታን የሚፈሩትን የሚያከብር፥
ቢጎዳም የማለውን የማይከዳ።
5 #
ዘፀ. 22፥24፤ 23፥8። ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥
በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል።
እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 15: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ