መዝሙር 148:11-13
መዝሙር 148:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የምድር ነገሥታት፥ አሕዛብም ሁሉ፥ አለቆች፥ የምድርም ፈራጆች ሁሉ፤ ጐልማሶችና ደናግል፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፤ የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግናሉ። ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ በሰማይና በምድር ያመሰግኑታል።
መዝሙር 148:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣ ወጣት ወንዶችና ደናግል፣ አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት። ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ።