መዝሙር 137:2-4
መዝሙር 137:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በቤተ መቅደስህም እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ስምህን አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና። በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኀይልህ በብዙ አጸናሃት። አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና።
Share
መዝሙር 137 ያንብቡመዝሙር 137:2-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን። የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤ የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን። የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!
Share
መዝሙር 137 ያንብቡ