መዝሙር 137:1-6
መዝሙር 137:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን። እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣ በገናዎቻችንን ሰቀልን። የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤ የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን። የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣ እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር! ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ ቀኝ እጄ ትክዳኝ። ሳላስታውስሽ ብቀር፣ ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ትጣበቅ።
መዝሙር 137:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን፥ ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን። እዚያ በገናዎቻችንን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቀልን። የማረኩንና ሥቃይ የሚያሳዩን ሰዎች በመዘመር እንድናስደስታቸው “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ለእኛ ዘምሩልን” አሉን። ለእግዚአብሔር መቅረብ የሚገባውን መዝሙር በባዕድ አገር እንዴት እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺን ብረሳሽ በገና የምጫወትበት ቀኝ እጄ ይክዳኝ፤ አንቺን ባላስታውስሽና ታላቅ ደስታዬ አድርጌ ባልቈጥርሽ ምላሴ ከትናጋዬ ይጣበቅ።
መዝሙር 137:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ የአፌን ነገር ሁሉ ሰምተኸኛልና፤ በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ። በቤተ መቅደስህም እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ እውነትህም ስምህን አመሰግናለሁ፥ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሃልና። በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፤ ነፍሴን በኀይልህ በብዙ አጸናሃት። አቤቱ፥ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ የአፍህን ቃል ሁሉ ሰምተዋልና። በእግዚአብሔርም ምስጋና ይዘምራሉ። የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና። እግዚአብሔር ከፍ ያለ ነውና፥ የተዋረዱትንም ይመለከታልና፤ ትቢተኛውንም ከሩቁ ያውቀዋል።
መዝሙር 137:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፥ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። በአኻያ ዛፎች ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን። የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን። የጌታን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ። ባላስታውስሽ፥ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፥ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።