መዝሙር 103:1-5
መዝሙር 103:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ መታመንንና የጌትነትን ክብር ለበስህ። ብርሃንን እንደ ልብስ ተጐናጸፍህ፤ ሰማይንም እንደ መጋረጃ ዘረጋህ፤ እልፍኙን በውኃ የሚሠራ፥ ደመናን መሄጃው የሚያደርግ፥ በነፋስ ክንፍም የሚሄድ፥ መላእክቱን መንፈስ፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው። ለዘለዓለም እንዳትናወጥ፥ ምድርን መሠረታት፥ አጸናትም።
Share
መዝሙር 103 ያንብቡመዝሙር 103:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤ ኀጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፣ ሕይወትሽን ከጥፋት ጕድጓድ የሚያድን፣ ምሕረትንና ርኅራኄን የሚያቀዳጅሽ፣ ጕልማሳነትሽም እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ፣ ምኞትሽን በበጎ ነገር የሚያረካ እርሱ ነው።
Share
መዝሙር 103 ያንብቡ