መዝሙር 102:18-28
መዝሙር 102:18-28 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤ “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቷልና፤ ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቷል፤ ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።” ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤ ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል። ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤ ዕድሜዬንም በዐጭሩ አስቀረው። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፤ ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ። አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤ እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ። አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም። የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤ ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”

መዝሙር 102:18-28 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ገና ያልተወለዱት ሰዎች እንዲያመሰግኑት ይህን እግዚአብሔር ያደረገውን ድንቅ ነገር ለሚመጣው ትውልድ ጻፉ። እግዚአብሔር በላይ ካለው ከቅዱስ ስፍራው ሆኖ ተመለከተ፤ ከሰማይ ወደ ምድር አየ። ይህንንም ያደረገው የእስረኞችን መቃተት ሰምቶ ሞት የተፈረደባቸውንም ነጻ ለማውጣት ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን ይነገራል፤ በኢየሩሳሌምም ይመሰገናል። ይህም የሚሆነው ሕዝቦችና መንግሥታት በአንድነት ተሰብስበው ለእግዚአብሔር በሚሰግዱበት ጊዜ ነው። እግዚአብሔር ገና ወጣት ሆኜ ሳለሁ ደካማ አደረገኝ፤ ሕይወቴንም አሳጠረ። “አምላክ ሆይ! የአንተ ዘመን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ስለ ሆነ ዕድሜዬን ሳላጠናቅቅ በግማሽ ዕድሜዬ አትውሰደኝ” አልኩ። አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ እነርሱ እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ እንደ መጐናጸፊያ ትለውጣቸዋለህ፤ ይወገዱማል። አንተ ግን ለዘለዓለም ያው ነህ፤ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም። የአገልጋዮችህ ልጆች በሰላም ይኖራሉ፤ ትውልዳቸውም በአንተ ዘንድ ጸንቶ ይኖራል።
መዝሙር 102:18-28 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም። ይህ ለሚመጣ ትውልድ ይጻፍ፥ የሚፈጠርም ሕዝብ ለጌታ እልል ይላል፥ ጌታ ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፥ የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፥ ሊገድሉ የተፈረደባቸውን ይፈታ ዘንድ፥ የጌታን ስም በጽዮን ምስጋናውንም በኢየሩሳሌም ይናገሩ ዘንድ፥ አሕዛብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ መንግሥታትም ለጌታ ይገዙ ዘንድ። በመንገዴ ጉልበቴ ዛለ፦ ዘመኔም አጠረ። ለእኔም ንገረኝ፥ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፥ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው። አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፥ ሁላቸውም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጣሉም፥ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።