መዝሙር 10:2-6
መዝሙር 10:2-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኀጢአተኞች እነሆ፥ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖቹን በስውር ይነድፉ ዘንድ። አንተ የሠራኸውን እነሆ፥ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ? እግዚአብሔር በቤተ መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዐይኖቹም ወደ ድሃ ይመለከታሉ፤ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ። እግዚአብሔር ጻድቁንና ኃጥኡን ይመረምራል፤ ዐመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል። ወጥመድ በኃጥኣን ላይ ይዘንባል፤ እሳትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፋንታ ነው።
መዝሙር 10:2-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ። ክፉ ሰው በልቡ ምኞት ይኵራራል፤ ስግብግቡን ይባርካል፤ እግዚአብሔርንም ይዳፈራል። ክፉ ሰው ከትዕቢቱ የተነሣ እግዚአብሔርን አይፈልግም፤ በሐሳቡም ሁሉ አምላክ የለም፤ መንገዱ ዘወትር የተሳካ ነው፤ ዕቡይ፣ ከሕግህም የራቀ ነው። በመሆኑም በጠላቶቹ ላይ ያፌዛል። በልቡም፣ “ከስፍራዬ የሚነቀንቀኝ የለም፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም መከራ አያገኘኝም” ይላል።
መዝሙር 10:2-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ክፉ ሰዎች ይታበያሉ፤ ድኾችንም ያሳድዳሉ፤ ለሌሎች በዘረጉት ወጥመድ ራሳቸው ይጠመዱ። ኃጢአተኛ በክፉ ምኞቱ ይመካል፤ ጌታ ሆይ! እነዚህ ስግብግብ ሰዎች ይጠሉሃል፤ ይሰድቡህማል። ክፉዎች ስለ እግዚአብሔር ግድ የላቸውም በትዕቢታቸውም እግዚአብሔር የለም ብለው ያስባሉ። ክፉ ሰው በሁሉ ነገር ይሳካለታል፤ የእግዚአብሔርን ፍርድ ግን ሊረዳ አይችልም፤ በጠላቶቹም ላይ ይሳለቃል። በሐሳቡ “የሚያነቃንቀኝ የለም፤ ምንም ችግር ሳያጋጥመኝ ሁልጊዜ እደሰታለሁ” ይላል።