መዝሙረ ዳዊት 10:2-6

መዝሙረ ዳዊት 10:2-6 መቅካእኤ

በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ። ክፉ በነፍሱ ፈቃድ ይኮራልና፥ ስግብግብም ይረግማል፥ ጌታንም ይንቃል። ክፉ በትዕቢቱ ጌታን አይፈልገውም፥ በሐሳቡ በሙሉ እግዚአብሔር የለም። መንገዱ ሁልጊዜ የጸና ነው፥ ፍርድህ ከእርሱ በላይ እጅግ ከፍ ያለ ነው፥ በጠላቶቹ ላይ ግን ይቀልዳል። በልቡ፦ “ለልጅ ልጅ አልታወክም ክፉም አያገኘኝም” ይላል።