ምሳሌ 24:3-7
ምሳሌ 24:3-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በዕውቀትም ይጸናል። በዕውቀት ከከበረውና ካማረው ሀብት ሁሉ ጓዳዎች ይሞላሉ። ጠቢብ ሰው ከብርቱ ይሻላል፥ ከታላቅ ርስትም ይልቅ ዕውቀት ያለው ይበልጣል። በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ ርዳታም ከምትመክር ልብ ጋር ይሆናል። ጥበብና መልካም ዕውቀት በብልሆች በር ትገኛለች፤ ብልሆች ከእግዚአብሔር ቃል አይርቁም።
Share
ምሳሌ 24 ያንብቡምሳሌ 24:3-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋልም ይጸናል፤ በዕውቀትም ውድና ውብ በሆነ ንብረት፣ ክፍሎቹ ይሞላሉ። ጠቢብ ሰው ታላቅ ኀይል አለው፤ ዕውቀት ያለውም ሰው ብርታትን ይጨምራል፤ ጦርነት ለመግጠም መልካም ምክር፣ ድል ለማድረግም ብዙ አማካሪዎች ያስፈልጋሉ። ጥበብ ለተላላ በጣም ሩቅ ናት፤ በከተማዪቱ በር ሸንጎ ላይም መናገር አይችልም።
Share
ምሳሌ 24 ያንብቡምሳሌ 24:3-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በጥበብ ቤት ይሠራል፤ በማስተዋልም ጸንቶ እንዲኖር ይደረጋል። ዕውቀት ሲኖር ቤት በከበሩና በሚያምሩ ዕቃዎች ይሞላል። ብርቱ ከመሆን ይልቅ ብልኅ መሆን ይሻላል፤ በእርግጥም ዕውቀት ከኀይል ይበልጣል፤ ለጦርነት ከመሰለፍህ በፊት በጥንቃቄ ዕቅድ ማውጣት ይኖርብሃል፤ ብዙ አማካሪዎች የምታገኝ ከሆነም ማሸነፍህ አይቀርም። ማስተዋል የጐደለው ሰው ጥበብን መገንዘብ አይችልም፤ ሰዎች ቁም ነገር ባለው ጉዳይ ላይ ሲወያዩ እርሱ የሚያቀርበው አስተያየት የለም።
Share
ምሳሌ 24 ያንብቡ