ነህምያ 9:5-38

ነህምያ 9:5-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ቀድምኤል፣ ባኒ፣ አሰበንያ፣ ሰራብያ፣ ሆዲያ፣ ሰበንያና ፈታያ፣ “ተነሥታችሁ ቁሙ፤ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የሚኖረውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱ” አሉ። “ክቡር ስምህ የተመሰገነ ይሁን፤ ከምስጋና ሁሉና ከውዳሴም በላይ ከፍ ከፍ ይበል። አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ። ሰማያትን፣ ከሰማያት በላይ ያሉትን ሰማያትና የከዋክብታቸውን ሰራዊት ሁሉ፣ ምድርንና በላይዋ ያለውን ሁሉ፣ ባሕሮችንና በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥረሃል። ለሁሉም ሕይወትን ትሰጣለህ፤ የሰማይ ሰራዊትም ይሰግዱልሃል። “አብራምን የመረጥኸውና ከከለዳውያን ዑር አውጥተህ አብርሃም የሚል ስም የሰጠኸው አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ። ልቡ ለአንተ የታመነ ሆኖ ስላገኘኸውም፣ የከነዓናውያንን የኬጢያውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የጌርጌሳውያንን ምድር ለዘሮቹ ለመስጠት ከርሱ ጋራ ቃል ኪዳን ገባህ፤ ጻድቅ ስለ ሆንህም የሰጠኸውን ተስፋ ጠበቅህ። “አንተ በግብጽ የአባቶቻችንን ሥቃይ አየህ፤ በቀይ ባሕርም ጩኸታቸውን ሰማህ። ታምራታዊ ምልክቶችንና ድንቆችን በፈርዖንና፣ በሹማምቱ ሁሉ፣ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ላክህ፤ ይህንም ያደረግኸው ግብጻውያን እንዴት በእብሪት እንዳስጨነቋቸው ስላወቅህ ነው። እስከ ዛሬም የሚጠራ ስም ለራስህ እንዲኖርህ አደረግህ። በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው። ቀን በደመና ዐምድ፣ በሚሄዱበት መንገድ ታበራላቸውም ዘንድ ሌሊት በእሳት ዐምድ መራሃቸው። “በሲና ተራራ ላይ ወረድህ፤ ከሰማይም ተናገርሃቸው። ትክክለኛ ደንቦችንና እውነተኛ ሕጎችን፣ መልካም ሥርዐቶችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው። የተቀደሰች ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፤ ትእዛዞችን፣ ሥርዐቶችንና ሕጎችን በባሪያህ በሙሴ አማካይነት ሰጠሃቸው። በተራቡ ጊዜ ከሰማይ መና ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ከዐለት ውሃ አፈለቅህላቸው፤ ልትሰጣቸው በተዘረጋች እጅ ወደማልህላቸውም ምድር ገብተው እንዲወርሱ አዘዝሃቸው። “እነርሱና አባቶቻችን ግን ትምክሕተኞችና ዐንገተ ደንዳኖች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም። ለመስማት አልፈለጉም፤ በመካከላቸውም ያደረግሃቸውን ታምራት ማስታወስ አልቻሉም። ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ በዐመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ። አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፣ ቸርና ርኅሩኅ፣ ለቍጣም የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ። ስለዚህ አልተውሃቸውም፤ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አቅልጠው፣ ‘ከግብጽ ያወጣህ አምላክ ይህ ነው’ ባሉና አስጸያፊ የስድብ ቃል በተናገሩ ጊዜ እንኳ አልተለየሃቸውም። “ከርኅራኄህ ብዛት የተነሣ በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፤ ቀን የደመናው ዐምድ በመንገዳቸው ላይ መምራቱን፣ ሌሊትም የእሳቱ ዐምድ በሚሄዱበት ላይ ማብራቱን አላቆመም። ያስተምራቸው ዘንድ ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናውን ከአፋቸው አልከለከልህም፤ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው። በምድረ በዳ አርባ ዓመት መገብሃቸው፤ ምንም ያጡት አልነበረም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸውም አላበጠም። “በሩቅ የሚገኙትን ድንበሮች እንኳ ሳይቀር፣ መንግሥታትንና አሕዛብን ሰጠሃቸው። የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፣ የባሳን ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። ወንዶች ልጆቻቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃቸው፤ አባቶቻቸው ገብተው እንዲወርሱ ወዳዘዝሃቸውም ምድር አገባሃቸው። በምድሪቱ ወንዶች ልጆቻቸው ገቡባት፤ ወረሷትም። በምድሪቱ ላይ ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያን በፊታቸው አንበረከክህ፤ ያሻቸውን ያደርጉባቸው ዘንድ ከነዓናውያንን ከንጉሦቻቸውና ከምድሪቱ ሕዝቦች ጋራ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። የተመሸጉ ከተሞቻቸውንና የሠባውን ምድር ያዙ፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሞሉ ቤቶቻቸውን፣ የተቈፈሩ የውሃ ጕድጓዶቻቸውን፣ የወይን ተክላቸውን፣ የወይራ ዛፎቻቸውንና ስፍር ቍጥር የሌላቸውን የፍሬ ዛፎች ያዙ። እስኪጠግቡ በሉ፤ ወፈሩም፤ በታላቅ በጎነትህም ደስ ተሠኙ። “ነገር ግን እንቢተኞች ሆኑ፤ ዐመፁብህም፤ ሕግህንም አሽቀንጥረው ጣሉ፤ ወደ አንተ እንዲመለሱ ሲያስጠነቅቋቸው የነበሩት ነቢያትህን ገደሉ፤ አስጸያፊ የስድብ ቃልም ተናገሩ። ስለዚህ ላስጨነቋቸው ጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። በተጨነቁ ጊዜ ግን ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም ከሰማይ ሰማሃቸው፤ ከርኅራኄህም ብዛት የተነሣ ከጠላቶቻቸው እጅ የሚያድኗቸውን ታዳጊዎች ሰጠሃቸው። “ነገር ግን ዕረፍት ባገኙ ጊዜ፣ በፊትህ ክፉውን ነገር እንደ ገና ፈጸሙ፤ ከዚያም ይገዟቸው ዘንድ በጠላቶቻቸው እጅ ጣልሃቸው፤ እንደ ገና ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ፣ ከሰማይ ሰማህ፤ በርኅራኄህም በየጊዜው ታደግሃቸው። “ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን እብሪተኞች ሆኑ። ትእዛዞችህንም አልፈጸሙም፤ ‘አንድ ሰው ቢፈጽማቸው በሕይወት የሚኖርባቸውን’ ሥርዐቶችህን ተላለፉ። እንቢተኞች ሆነው ጀርባቸውን አዞሩብህ፤ ዐንገታቸውን አደነደኑ፤ መስማትም አልፈለጉም። ብዙ ዘመን ታገሥሃቸው፤ በነቢያትህ አማካይነት በመንፈስህ አስጠነቀቅሃቸው። ነገር ግን አላደመጡህም፤ ከዚህም የተነሣ ጎረቤቶቻቸው ለሆኑ አሕዛብ አሳልፈህ ሰጠሃቸው። አንተ ግን ቸርና መሓሪ አምላክ ነህና ከምሕረትህ ብዛት የተነሣ፣ ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፤ አልተውሃቸውምም። “አሁንም አምላካችን ሆይ፤ ቃል ኪዳንህንና ዘላለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅ፣ ኀያልና የተፈራህ አምላክ ሆይ፤ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችንና በመሪዎቻችን፣ በካህናታችንና በነቢያታችን፣ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ የደረሰው ይህ ሁሉ መከራ በፊትህ እንደ ቀላል ነገር አይታይ። በደረሰብን ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ እኛ በደለኞች ነን፤ አንተ ግን ትክክለኛውን አደረግህ። ነገሥታታችን፣ መሪዎቻችን፣ ካህናታችንና አባቶቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ ትእዛዞችህን ወይም የሰጠሃቸውን ማስጠንቀቂያዎች አልሰሙም። በገዛ መንግሥታቸው፣ በሰጠሃቸው ታላቅ በጎነትህና በፊታቸውም ባዘጋጀህላቸው ሰፊና ለም ምድር እንኳ፣ አንተን አላገለገሉም፤ ከክፉ መንገዳቸውም አልተመለሱም። “እነሆ፤ ዛሬም ባሮች ነን፤ አባቶቻችን ፍሬዋንና በረከቷን እንዲበሉ በሰጠሃቸው ምድር ባሮች ነን። ከኀጢአታችን የተነሣ የተትረፈረፈው መከር ሲሳይ የሆነው በላያችን ላስቀመጥሃቸው ነገሥታት ነው፤ እነርሱም ደስ እንዳሰኛቸው በሰውነታችንና በቀንድ ከብቶቻችን ላይ ያዝዛሉ። እኛም በታላቅ ጭንቀት ውስጥ እንገኛለን። “ከዚህ ሁሉ የተነሣም ጽሑፍ ላይ በማስፈር ግዴታ የምንገባበትን የውል ስምምነት እናደርጋለን፤ መሪዎቻችን፣ ሌዋውያናችንና ካህናታችንም ማኅተሞቻቸውን ያኖሩበታል።”

ነህምያ 9:5-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሌዋውያኑም ኢያሱ፥ ቀድምኤል፥ ባኒ፥ አሰበንያ፥ ሰራብያ፥ ሆዲያ፥ ሰበንያ፥ ፈታያ እንዲህ አሉ፦ ቆማችሁ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችንን እግዚአብሔርን ባርኩ። እንዲህም በሉ፦ በበረከትና በምስጋና ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው ክቡር ስምህ ይባረክ። አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፥ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፥ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ። አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ፥ አብራምን መረጥህ፥ ከዑር ከላውዴዎንም አወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም አልኸው፥ ልቡም በፊትህ የታመነ ሆኖ አገኘኸው፥ የከነዓናዊውንና የኬጢያዊውን የአሞራዊውንም የፌርዛዊውንም የኢያቡሳዊውንም የጌርጌሳዊውንም ምድር ለእርሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ፥ አንተም ጻድቅ ነህና ቃልህን ፈጸምህ። በግብጽም ሳሉ የአባታችንን መከራ አየህ፥ በኤርትራ ባሕርም ሳሉ ጩኸታቸውን ሰማህ፥ እንደ ታበዩባቸውም አውቀህ ነበርና በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ በምድሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምልክትና ተአምራት አሳየህ፥ ዛሬም እንደ ሆነው ስምህን አስጠራህ። ከፊታቸውም ባሕሩን ከፈልህ፥ በባሕሩም መካከል በደረቅ አለፉ፥ ጠላቶቻቸውን ግን ድንጋይ ለጥልቅ ውኃ እንዲጣል በቀላይ ውስጥ ጣልሃቸው። የሚሄዱበትንም መንገድ ታበራላቸው ዘንድ በቀን በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ መራሃቸው። ወደ ሲናም ተራራ ወረድህ፥ ከሰማይም ተናገርሃቸው፥ ቅኑን ፍርድና እውነቱን ሕግ መልካሙንም ሥርዓትና ትእዛዝ ሰጠሃቸው፥ የተቀደሰውንም ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፥ ትእዛዝንና ሥርዓትን ሕግንም በባሪያህ በሙሴ እጅ አዘዝሃቸው። ለራባቸውም ከሰማይ እንጀራ ሰጠሃቸው፥ ለጥማታቸውም ከዓለቱ ውኃ አመጣህላቸው፥ ወደ ማልህላቸውም ምድር ገብተው ይወርሱ ዘንድ አዘዝሃቸው። ነገር ግን እነርሱና አባቶቻችን ታበዩ፥ አንገታቸውንም አደነደኑ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ለመስማትም እንቢ አሉ፥ ያደረግህላቸውንም ተአምራት አላሰቡም፥ አንገታቸውንም አደነደኑ፥ በዓመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ይመለሱ ዘንድ አለቃ አደረጉ፥ አንተ ግን ይቅር ባይ፥ ቸርና መሐሪ አምላክ፥ ለቁጣም የምትዘገይ፥ ምሕረትንም የምታበዛ ነህ፥ አልተውሃቸውም። ቀልጦ የተሠራውንም እምቦሳ አድርገው፦ ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው ባሉ ጊዜ፥ እጅግም ባስቈጡህ ጊዜ፥ አንተ በምሕረትህ ብዛት በምድረ በዳ አልተውሃቸውም፥ በመንገድም ይመራቸው ዘንድ የደመና ዓምድ በቀን፥ የሚሄዱበትንም መንገድ ያበራላቸው ዝነድ የእሳት ዓምድ በሌሊት ከእነርሱ አልራቀም። ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው፥ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልህም፥ ለጥማታቸውም ውኃ ሰጠሃቸው። አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብሃቸው፥ ምንም አላጡም፥ ልብሳቸውም አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም። መንግሥታትንና አሕዛብን ከፍለህ ሰጠሃቸው፥ የሐሴቦንን ንጉሥ የሴዎንን ምድር፥ የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ምድር ወረሱ። ልጆቻቸውንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛህ፥ ይገቡና ይወርሱ ዘንድ ለአባቶቻቸው ወደ ተናገርህላቸውም ምድር አገባሃቸው። ልጆቹም ገብተው ምድሩን ወረሱ፥ የምድሩን ሰዎች ከነዓናውያንን በፊታቸው አዋረድህ፥ የሚወድዱትንም ነገር ያደረጉባቸው ዘንድ እነርሱንና ነገሥታቶቻቸውን የምድሩንም አሕዛብ በእጃቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። ምሽጎቹንም ከተሞች የሰባውንም ምድር ወሰዱ፥ መልካሙን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጕድጓዶች፥ ወይኖቹንና ወይራዎቹን ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፥ በሉም፥ ጠገቡም፥ ወፈሩም፥ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው። ነገር ግን እንቢተኞች ነበሩ፥ ዐመፁብህም፥ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፥ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፥ እጅግም አስቈጡህ። ስለዚህ ለጠላቶቻቸው እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፥ አስጨነቁአቸውም፥ በመከራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፥ ከሰማይም ሰማሃቸው፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳኑአቸውን ታዳጊዎችን ሰጠሃቸው። ባረፉም ጊዜ ተመልሰው በፊትህ ክፉ አደረጉ፥ በጠላቶቻቸው እጅ ተውሃቸው፥ ገዙአቸውም፥ ተመልሰውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰማይ ሰማሃቸው፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ታደግሃቸው፥ ወደ ሕግህም ትመልሳቸው ዘንድ አስመሰከርህባቸው፥ ነገር ግን ታበዩ፥ ትእዛዝህንም አልሰሙም፥ ሰውም ባደረገው ጊዜ በሕይወት የሚኖርበትን ፍርድህን ተላለፉ፥ ትከሻቸውንም ሰጡ፥ አንገታቸውን አደነደኑ፥ አልሰሙምም። ነገር ግን ብዙ ዓመታት ታገሥሃቸው፥ በነቢያትህም እጅ በመንፈስህ መሰከርህባቸው፥ አላደመጡም፥ ስለዚህም በምድር አሕዛብ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው። ነገር ግን አንተ ቸርና መሐሪ አምላክ ነህና በምሕረትህ ብዛት ፈጽመህ አላጠፋሃቸውም፥ አልተውሃቸውምም። አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ቃል ኪዳንና ምሕረትን የምትጠብቅ ታላቅና ኃያል የተፈራኸውም አምላክ ሆይ፥ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛና በነገሥታቶቻችን በአለቆቻችንም በካህናቶቻችንም በነቢያቶቻችንም በአባቶቻችንም በሕዝብህ ሁሉ ላይ የደረሰው መከራ ሁሉ በፊትህ ጥቂት መስሎ አይታይህ። በደረሰብንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፥ አንተ እውነት አድርገሃልና፥ እኛም ኃጢአት አድርገናል። ነገሥታቶቻችንም አለቆቻችንም ካህናቶቻችንም አባቶቻችንም ሕግህን አልጠበቁም፥ የመሰከርህባቸውንም ትእዛዝህንና ምስክርህን አልሰሙህም። በመንግሥታቸውም በሰጠሃቸውም ታላቅ በጎነትህ፥ በፊታቸውም በሰጠኸው በሰባው ምድር አላመለኩህም፥ ከክፉም ሥራቸው አልተመለሱም። እነሆ፥ ዛሬ ባሪያዎች ነን፥ ፍሬዋንና በረከትዋን ይበሉ ዘንድ ለአባቶቻችን በሰጠሃት ምድር፥ እነሆ፥ በእርስዋ ባሪያዎች ነን፥ ስለ ኃጢአታችንም ለሾምህብን ነገሥታት በረከትዋን ታበዛለች፥ ሰውነታችንንም ይገዛሉ፥ በእንስሶቻችንም የሚወድዱትን ያደርጋሉ፥ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን። ስለዚህም ሁሉ የታመነውን ቃል ኪዳን አድርገን እንጽፋለን፥ አለቆቻችንም ሌዋውያኖቻችንም ካህናቶቻችንም ያትሙበታል።

ነህምያ 9:5-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢያሱ፥ ቃድሚኤል፥ ባኒ፥ ሐሸባንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሸባንያና ፐታሕያ ተብለው የሚጠሩት ሌዋውያን፦ “ተነሥታችሁ በመቆም ዘለዓለማዊውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ከምስጋናና ከበረከት ሁሉ በላይ፥ ከፍ ከፍ ይበል! በሉ” አሉአቸው። ከዚህም ሁሉ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አምላክ አንተ ብቻ ነህ፤ ሰማያትን፥ የሰማያትንም ሰማያት ከነሠራዊታቸው፥ ምድርንና በእርስዋም ላይ የሚገኘውን ሁሉ፥ ባሕሮችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ፥ ፈጠርክ፤ ለሁሉም ሕይወትን ሰጠሃቸው፤ የሰማይ ሠራዊት ይሰግዱልሃል። የባቢሎን ክፍል ከሆነችው ዑር፥ አብራምን መርጠህ ያመጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም ያልከው፥ አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ። እርሱም ለአንተ ታማኝ እንደ ሆነ ተመልክተህ፥ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳንን አደረግህ፤ ከነዓናውያን፥ ሒታውያን፥ አሞራውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ኢያቡሳውያንና ጌርጌሳውያን የሚኖሩባትንም የከነዓንን ምድር ለዘሮቹ መኖሪያ ርስት አድርገህ ልትሰጠው ቃል ገባህለት፤ አንተ ታማኝ ስለ ሆንክ ቃል ኪዳንህን አጽንተህ ጠብቀሃል። “አንተ የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ የደረሰባቸውን መከራ አየህ፤ ቀይ ባሕር አጠገብ ሆነው እንድትረዳቸው ያቀረቡትን ልመና ሰማህ። በግብጽ ንጉሥ ላይ በባለሥልጣኖቹና በምድሩ በሚኖሩትም ሕዝብ ሁሉ ላይ ድንቅ ተአምራትን ገልጠህ አሳየህ። ይህንንም ያደረግኸው የቀድሞ አባቶቻችን እንዴት እንደሚጨቈኑ በማየትህ ነው፤ ይህንንም በማድረግህ እስከ ዛሬ ድረስ ዝናህ የገነነ ሆኖአል። ባሕሩን በፊታቸው ለሁለት ከፈልክ፤ በደረቅ ምድርም ተሻገሩ፤ ድንጋይ ወደ ጥልቅ ባሕር እንደሚጣል፥ እነርሱን ያሳድዱ የነበሩትንም ወደ ጥልቁ ጣልካቸው። በቀን በደመና ዐምድ መራሃቸው፤ በሌሊትም መንገዳቸውን በእሳት ዐምድ አበራህላቸው። ወደ ሲና ተራራ ወርደህ ከሰማይ ሕዝብህን አነጋገርካቸው፤ ትክክለኛና ፍትሓዊ ሕግንና ሥርዓትን፥ መልካም የሆኑትን ደንቦችንና ትእዛዞችን ሰጠሃቸው። የተቀደሰውን ሰንበትህንም እንዲያውቁ አደረግሃቸው፤ በአገልጋይህም በሙሴ አማካይነት ትእዛዞችህን፥ ድንጋጌህንና ሕጎችህን ሰጠሃቸው። “በተራቡም ጊዜ ምግብን ከሰማይ ሰጠሃቸው፤ በተጠሙም ጊዜ ውሃን ከአለት አፈለቅህላቸው፤ ለእነርሱ ልትሰጣቸው ቃል የገባህላቸውንም ምድር በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉ ዘንድ አዘዝካቸው። ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ትዕቢተኞችና እልኸኞች ሆኑ፤ ትእዛዞችህንም አልጠበቁም፤ ታዛዦችም አልሆኑም። በመካከላቸው ያደረግኸውን ተአምራት ሁሉ ረሱ፤ እልኸኞችም ሆነው፤ ወደ ግብጹ ባርነታቸው እንዲመልሳቸው መሪ መረጡ። አንተ ግን በፍቅር የተሞላህ፥ ለቊጣ የዘገየህ፥ ይቅር ባይ፥ ቸርና መሐሪ አምላክ በመሆንህ አልተውካቸውም። በጥጃ አምሳል ለራሳቸው ጣዖትን ሠርተው፥ ‘ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላክ ይህ ነው!’ አሉ፤ በአንተ ላይም ከፍተኛ የስድብን ቃል እንኳ ተናገሩ፤ ምሕረትህም ታላቅ በመሆኑ በዚያ ምድረ በዳ ይጠፉ ዘንድ አልተውካቸውም፤ ነገር ግን የደመናው ዐምድ በቀን ይመራቸው ነበር፤ የእሳቱ ዐምድ በሌሊት ያበራላቸው ነበር። የሚያስተምራቸውን ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ የሚመገቡትን መና፥ የሚጠጡትንም ውሃ ሰጠሃቸው። አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ረዳሃቸው፤ ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ምንም አላሳጣሃቸውም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸው አላበጠም። “የአሕዛብን መንግሥታትና ነገሥታትን ድል ነሥተው፥ ከምድራቸው አዋሳኞች የሆኑትን ጠረፎች እንዲይዙ አደረግህ፤ ሲሖን የተባለ ንጉሥ ይገዛት የነበረችውን ሐሴቦን ተብላ የምትጠራውን ምድር፥ በድል አድራጊነት ያዙ፤ ዖግ የተባለው ንጉሥ ይገዛት የነበረችውንም የባሳንን ምድር ወረሱ። ብዛታቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የሆኑ ልጆችን ሰጠሃቸው፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ትሰጣቸው ዘንድ ቃል የገባህላቸውን ምድር፥ በድል አድራጊነት እንዲይዙ ፈቀድክላቸው። ልጆቻቸው የከነዓንን ምድር ድል አድርገው ያዙ፤ በዚያ ይኖሩ የነበሩትንም ሕዝብ በፊታቸው ሆነህ አንተ ድል ነሣህላቸው፤ በነገሥታትና በዚያች የከነዓን አገር ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ሁሉ ያደርጉባቸው ዘንድ ኀይልን ሰጠሃቸው። የተመሸጉ ከተሞችንና፥ ለም የሆነችውን ምድር፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሟሉ ቤቶችን፥ የውሃ ጒድጐዶችንና የወይን ተክል ቦታዎችን የወይራና ብዙ የፍሬ ዛፎችን ወረሱ፤ በልተው በመጥገብም ሰውነታቸውን አወፈሩ፤ በቸርነትህ በሰጠሃቸው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰቱ። “ነገር ግን እነርሱ በአንተ ላይ ዐምፀው ለቃልህ አንታዘዝም አሉ፤ ሕግህንም ላለመስማት ፊታቸውን መለሱ፤ በማስጠንቀቅ ወደ አንተ እንዲመለሱ ያስተማሩአቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ በየጊዜውም በአንተ ላይ ክፉ የስድብ ቃል ተናገሩ፤ ስለዚህም ጠላቶቻቸው እነርሱን ድል አድርገው ይገዙአቸው ዘንድ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ እነርሱም አስጨነቁአቸው። በችግራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ አንተም በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ፥ ከጠላቶቻቸው የሚታደጉ መሪዎችን ላክህላቸው። ነገር ግን ሰላም ባገኙ ጊዜ እንደገና ኃጢአት ሠሩ፤ አንተም እንደገና ድል ለሚነሡ ጠላቶቻቸው ተውካቸው እነርሱም ገዙአቸው፤ ነገር ግን አንተ እንድትረዳቸው እንደገና በጠየቁ ጊዜ በሰማይ ሆነህ ሰማሃቸው፤ ከርኅራኄህም የተነሣ በየጊዜው ታደግኻቸው። እነርሱም ወደ ሕግህ እንዲመለሱ አስጠነቀቅኻቸው፤ በትዕቢታቸው ግን ትእዛዞችህን ናቁ፤ ቢፈጽሙአቸው ሕይወት በሚሰጡት ሕጎችህ ላይ ኃጢአት ሠሩ። በልበ ደንዳናነት ፊታቸውን አዞሩ፤ በእልኸኛነታቸውም እምቢተኞች ሆኑ። አንተም ለብዙ ዓመቶች ታገሥካቸው፤ ያስተምሩአቸውም ዘንድ ነቢያትን በመንፈስህ አስነሣህላቸው፤ ነገር ግን እነርሱ አላዳመጡም፤ ስለዚህም ለጐረቤት ሕዝቦች ድል እንዲነሡአቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው። እንደገናም ከምሕረትህ ታላቅነት የተነሣ አልተውካቸውም፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ አምላክም ስለ ሆንክ አልደመሰስካቸውም። “ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ። እኛን ለመቅጣት ያደረግኸው ውሳኔ ትክክል ነው፤ እኛ በደል ብንሠራም፥ አንተ በታማኝነትህ እንደ ጸናህ ነህ። የቀድሞ አባቶቻችን፥ ንጉሦቻችን፥ መሪዎቻችንና ካህኖቻችን ሕግህን አልጠበቁም፤ የሰጠሃቸውን ትእዛዞች ማስጠንቀቂያዎች አላዳመጡም። መንግሥታቸው በሰጠሃቸው ቸርነት፥ በሰጠሃቸው ሰፊና ለም መሬት፥ ይደሰቱ በነበረ ጊዜ እንኳ፥ አንተን አላመለኩም፥ ከኃጢአታቸውም አልተመለሱም። ስለዚህም አንተ ለአባቶቻችን ፍሬዋን እንዲበሉና በመልካም ነገሮችም እንዲደሰቱ፥ በሰጠሃቸው ምድር ላይ እነሆ፥ ዛሬ እኛ ባሪያዎች ሆነናል። እኛም ኃጢአት በመሥራታችን ምክንያት ስላሳዘንክ፥ የምድሪቱንም በረከት በእኛ ላይ ገዢዎች አድርገህ ላስነሣሃቸው ነገሥታት ገቢ ይሆናል፤ እነርሱ በእኛና በእንስሶቻችን ላይ ደስ ያሰኛቸውን ነገር ሁሉ ይፈጽማሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ በታላቅ ጭንቀት ላይ እንገኛለን።” ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እኛ የጽሑፍ ስምምነት ለማድረግ ወሰንን፤ በስምምነቱም ጽሑፍ ላይ መሪዎቻችን፥ ሌዋውያኖቻችንና ካህናቶቻችን ማኅተማቸውን አኖሩበት።

ነህምያ 9:5-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና ቀድ​ም​ኤል፥ እን​ዲህ አሉ፥ “ቆማ​ችሁ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ። የከ​በረ ስሙ​ንም አመ​ስ​ግኑ፤ በበ​ረ​ከ​ትና በም​ስ​ጋ​ናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት።” ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ። አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነህ፤ አብ​ራ​ምን መረ​ጥህ፤ ከዑር ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም አወ​ጣ​ኸው፤ ስሙ​ንም አብ​ር​ሃም አል​ኸው፤ ልቡም በፊ​ትህ የታ​መነ ሆኖ አገ​ኘ​ኸው፤ የከ​ነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንና የኬ​ጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ የጌ​ር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ምድር ለእ​ር​ሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግህ፤ አን​ተም ጻድቅ ነህና ቃል​ህን አጸ​ናህ። “በግ​ብ​ጽም ሳሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንን መከራ አየህ፤ በኤ​ር​ትራ ባሕ​ርም ሳሉ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማህ፤ እንደ ታበ​ዩ​ባ​ቸ​ውም ዐው​ቀህ ነበ​ርና በፈ​ር​ዖ​ንና በባ​ሪ​ያ​ዎቹ ሁሉ፥ በም​ድ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ተአ​ም​ራ​ትን አሳ​የህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው ስም​ህን አስ​ጠ​ራህ። ከፊ​ታ​ቸ​ውም ባሕ​ሩን ከፈ​ልህ፤ በባ​ሕ​ሩም መካ​ከል በደ​ረቅ ዐለፉ፤ የተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውን ግን ድን​ጋይ በጥ​ልቅ ውኃ እን​ዲ​ጣል በቀ​ላይ ውስጥ ጣል​ሃ​ቸው። የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ታበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ ቀን በደ​መና ዐምድ፥ ሌሊ​ትም በእ​ሳት ዐምድ መራ​ሃ​ቸው። ወደ ሲናም ተራራ ወረ​ድህ፤ ከሰ​ማ​ይም ተና​ገ​ር​ሃ​ቸው፤ ቅኑን ፍር​ድና እው​ነ​ቱን ሕግ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ሥር​ዐ​ትና ትእ​ዛዝ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ሰን​በ​ት​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝ​ንና ሥር​ዐ​ትን፥ ሕግ​ንም በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው። ለራ​ባ​ቸ​ውም ከሰ​ማይ እን​ጀ​ራን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ከዓ​ለቱ ውኃን አወ​ጣ​ህ​ላ​ቸው፤ ትሰ​ጣ​ቸ​ውም ዘንድ እጅ​ህን የዘ​ረ​ጋ​ህ​ባ​ትን ምድር ገብ​ተው ይወ​ር​ሷት ዘንድ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው። “ነገር ግን እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ችን ታበዩ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም፥ ለመ​ስ​ማ​ትም እንቢ አሉ፤ ያደ​ረ​ግ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንም ተአ​ም​ራት አላ​ሰ​ቡም፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ ለባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም ወደ ግብፅ ይመ​ለሱ ዘንድ አለ​ቃን ሾሙ፤ አንተ ግን መሓ​ሪና ይቅር ባይ አም​ላክ፥ ለቍ​ጣም የም​ት​ዘ​ገይ፥ ምሕ​ረ​ት​ንም የም​ታ​በዛ ነህ፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም። ዳግ​መ​ኛም ቀልጦ የተ​ሠ​ራ​ውን እን​ቦሳ አድ​ር​ገው፦ ‘ከግ​ብፅ ያወ​ጡን አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን እሊህ ናቸው’ አሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ፤ አንተ ግን ምሕ​ረ​ትህ ብዙ ነውና በም​ድረ በዳ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ውም፤ በመ​ን​ገ​ድም ይመ​ራ​ቸው ዘንድ የደ​መና ዓም​ድን በቀን፥ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያበ​ራ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ሳት ዓም​ድን በሌ​ሊት ከእ​ነ​ርሱ አላ​ራ​ቅ​ህም። ያስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውም ዘንድ መል​ካ​ሙን መን​ፈ​ስ​ህን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ መና​ህ​ንም ከአ​ፋ​ቸው አል​ከ​ለ​ከ​ል​ህም፤ ለጥ​ማ​ታ​ቸ​ውም ውኃን ሰጠ​ሃ​ቸው። አርባ ዓመ​ትም በም​ድረ በዳ መገ​ብ​ሃ​ቸው፤ ምንም አላ​ሳ​ጣ​ሃ​ቸ​ውም፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም አላ​ረ​ጀም፤ እግ​ራ​ቸ​ውም አላ​በ​ጠም። “መን​ግ​ሥ​ታ​ት​ንና አሕ​ዛ​ብን ዕድል ፈንታ አድ​ር​ገህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን ምድር፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን ምድር ወረሱ። ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛህ፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ተና​ገ​ር​ህ​ላ​ቸው ምድር አገ​ባ​ሃ​ቸው። እነ​ር​ሱም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች በፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ሃ​ቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ነገር ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ር​ሱ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የም​ድ​ሩ​ንም አሕ​ዛብ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው። ምሽ​ጎ​ቹ​ንም ከተ​ሞች፥ መል​ካ​ምን ነገር የሞ​ሉ​ትን ቤቶች፥ የተ​ማ​ሱ​ት​ንም ጕድ​ጓ​ዶች፥ የወ​ይ​ኖ​ቹ​ንና የወ​ይ​ራ​ዎ​ቹን ቦታ​ዎች፥ ብዙ​ዎ​ቹ​ንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገ​ቡም፤ ወፈ​ሩም፤ በታ​ላቅ በጎ​ነ​ት​ህም ደስ አላ​ቸው። “ነገር ግን ተመ​ል​ሰው ዐመ​ፁ​ብህ፤ ሕግ​ህ​ንም ወደ ኋላ​ቸው ጣሉት፤ ወደ አን​ተም ይመ​ለሱ ዘንድ የመ​ሰ​ከ​ሩ​ባ​ቸ​ውን ነቢ​ያ​ት​ህን ገደሉ፤ እጅ​ግም አስ​ቈ​ጡህ። ስለ​ዚህ በሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው ሰዎች እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው፤ አስ​ጨ​ነ​ቋ​ቸ​ውም፤ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰ​ማ​ይም ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታዳ​ጊ​ዎ​ችን ሰጠ​ሃ​ቸው፤ ከሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ውም እጅ አዳ​ን​ሃ​ቸው። ባረ​ፉም ጊዜ ተመ​ል​ሰው በፊ​ትህ ክፉ አደ​ረጉ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እጅ ተው​ሃ​ቸው፤ ገዙ​አ​ቸ​ውም፤ ተመ​ል​ሰ​ውም ወደ አንተ በጮኹ ጊዜ ከሰ​ማይ ሰማ​ሃ​ቸው፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ታደ​ግ​ሃ​ቸው፤ ወደ ሕግ​ህም ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ አስ​መ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙ​ህም፤ ሰውም ባደ​ረ​ገው ጊዜ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና ፍር​ድ​ህን ተላ​ለፉ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውን ሰጡ፤ አን​ገ​ታ​ቸ​ው​ንም አደ​ነ​ደኑ፤ አል​ሰ​ሙ​ምም። ነገር ግን ብዙ ዓመ​ታት ታገ​ሥ​ሃ​ቸው፤ በነ​ቢ​ያ​ት​ህም እጅ በመ​ን​ፈ​ስህ መሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸው፤ አላ​ደ​መ​ጡም፤ ስለ​ዚ​ህም በም​ድር አሕ​ዛብ እጅ አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው። ነገር ግን አንተ ኀያል፥ ቸርና መሓሪ አም​ላክ ነህና በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ፈጽ​መህ አላ​ጠ​ፋ​ሃ​ቸ​ውም፤ አል​ተ​ው​ሃ​ቸ​ው​ምም። “አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ ታላ​ቅና ኀያል ጽኑ​ዕና የተ​ፈ​ራ​ኸው አም​ላክ ሆይ፥ ከአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ በእ​ኛና በነ​ገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ በአ​ለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ በካ​ህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በነ​ቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ በሕ​ዝ​ብህ ሁሉ ላይ የደ​ረ​ሰው መከራ ሁሉ በፊ​ትህ ጥቂት መስሎ አይ​ታ​ይህ። በደ​ረ​ሰ​ብ​ንም ነገር ሁሉ አንተ ጻድቅ ነህ፤ አንተ እው​ነት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ እኛም እጅግ በድ​ለ​ና​ልና። ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ችን፥ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ​ህን አል​ጠ​በ​ቁም፤ ትእ​ዛ​ዝ​ህ​ንና የመ​ሰ​ከ​ር​ህ​ባ​ቸ​ውን ምስ​ክ​ር​ህ​ንም አል​ሰ​ሙም። በመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህም በሰ​ጠ​ሃ​ቸው ታላቅ በጎ​ነ​ትህ፥ በፊ​ታ​ቸ​ውም በሰ​ጠ​ሃ​ቸው በሰ​ፊ​ውና በሰ​ባው ምድር አል​ተ​ገ​ዙ​ል​ህም፤ ከክ​ፉም ሥራ​ቸው አል​ተ​መ​ለ​ሱም። እነሆ፥ ዛሬ ባሪ​ያ​ዎች ነን፤ ፍሬ​ዋ​ንና በረ​ከ​ቷን ይበሉ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ሃት ምድር እነሆ፥ በእ​ር​ስዋ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ለሾ​ም​ህ​ብን ነገ​ሥ​ታት በረ​ከ​ቷን ታበ​ዛ​ለች፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም ይገ​ዛሉ፤ በእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ንም የሚ​ወ​ድ​ዱ​ትን ያደ​ር​ጋሉ፤ እኛም በጽኑ መከራ ላይ ነን። ስለ​ዚ​ህም ሁሉ የታ​መ​ነ​ውን ቃል ኪዳን አድ​ር​ገን እን​ጽ​ፋ​ለን፤ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኖ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ያት​ሙ​በ​ታል።”