ነህምያ 3:15
ነህምያ 3:15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የምጽጳ አውራጃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም “የምንጭ በር” ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሠራ፤ መልሶ ከሠራም በኋላ ከድኖ መዝጊያዎቹን በየቦታቸው አኖረ፤ መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹንም አበጀ። “የንጉሥ አትክልት ቦታ” ተብሎ በሚጠራው አጠገብ የሚገኘውን የሼላን መዋኛ ግንብም፣ ከዳዊት ከተማ ጀምሮ ቍልቍል እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ መልሶ ሠራ።
Share
ነህምያ 3 ያንብቡነህምያ 3:15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የመሴፋም ገዢ የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፤ ሠራው፤ ከደነውም፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፤ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የመዋኛ ቅጥር ሠራ።
Share
ነህምያ 3 ያንብቡነህምያ 3:15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የምጽጳም ግዛት አለቃ የኮልሖዜ ልጅ ሰሎም የምንጩን በር አደሰ፥ ሠራው፥ ከደነውም፥ ሳንቃዎቹንም አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ፥ ከዳዊትም ከተማ እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ በንጉሡ አትክልት አጠገብ ያለውን የሼላን መዋኛ ቅጥር ሠራ።
Share
ነህምያ 3 ያንብቡ